Kishore Kumar Hits

Endale Woldegiorgis - Zelalemawi lyrics

Artist: Endale Woldegiorgis

album: Zelalemawi


የማታረጀው ፡ ማትቀደደው
ሀሩር ፡ ሲመጣ ፡ ማትቀየረው
ዘላለማዊው ፡ ልብሴ ፡ የኔነቴ: ውበት:ግርማ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ መደምደሚያ
ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ 2X
አንተን ፡ ለብሶ ፡ ተጐናፅፎ
እራቁቱን ፡ ማንስ ፡ ቀርቶ
የለበሰህ ፡ ከበረ ፡ እንጂ
መቼ ፡ ቆመ ፡ ውርደት ፡ ደጅ
አንተን ፡ ያለ ፡ የታደለ ፡ እራቆቱ ፡ ተሸፈነ 2X
ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ 2X
ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ሚለበስ ፡ ሁሉ
የማያዛልቅ ፡ ቅጠል ፡ መሆኑ
የተረዳ ፡ ሰው ፡ ሌላውን ፡ አውልቆ
አንተን ፡ ሲለብሰህ ፡ አዳኙን ፡ አውቆ
የሞትን ፡ ነፋስ ፡ ብርድን ፡ አይፈራ ፡ የዘላለሙን ፡ ለብሶሃልና 2X
ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ 2X
የማታረጀው ፡ ማትቀደደው
ሀሩር ፡ ሲመጣ ፡ ማትቀየረው
ዘላለማዊው ፡ ልብሴ ፡ የኔነቴ: ውበት ፡ ግርማ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ መደምደሚያ
ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ 2X

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists