Kishore Kumar Hits

Yohanes John Girma - Kesemayat Belay lyrics

Artist: Yohanes John Girma

album: Erste Neh, Vol. 1


ሠማይን ፡ ዘርግተህ ፡ እንዲህ ፡ አንጣለሃል
ከትልቅነቱ ፡ ብዛት ፡ የሰው ፡ ስሌት ፡ ያልፋል
አንተ ፡ የሰራኸው
በስንዝር ፡ የለካኸው
ይህ ፡ ሰማይ ፡ ትልቅ ፡ ከተባለ
አንተ ፡ ምን ፡ ትባላለህ
አዝ፦ ከሰማያት ፡ በላይ ፡ በላይ
ከምድርም ፡ በላይ ፡ በላይ
ከፍጥረታት ፡ በላይ ፡ በላይ
አንት ፡ ትልቅ ፡ ነህ
አንት ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፫x)
በምድር ፡ የሰው ፡ ቁጥር ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው
ከአዳም ፡ ጀምሮ ፡ እስካሁን ፡ የኖረው
በፊት ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ ሲታይ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
በገንቦ ፡ እንዳለች ፡ ትንሽ ፡ ጠብታ
ምትገርም ፡ ነህ ፡ ጌታ
አዝ፦ ከሰማያት ፡ በላይ ፡ በላይ
ከምድርም ፡ በላይ ፡ በላይ
ከፍጥረታት ፡ በላይ ፡ በላይ
አንት ፡ ትልቅ ፡ ነህ
አንት ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፫x)
በምድር ፡ ለሚኖሩ ፡ ምድር ፡ ሰፊ ፡ እርስት ፡ ናት
ስፋቷን ፡ በብዙ ፡ ቁጥር ፡ የሚያሰሏት
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታዬ ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ ፡ ነህ
በክበቦቿ ፡ ላይ ፡ ትቀመጣለህ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ላድርግህ
አዝ፦ ከሰማያት ፡ በላይ ፡ በላይ
ከምድርም ፡ በላይ ፡ በላይ
ከፍጥረታት ፡ በላይ ፡ በላይ
አንት ፡ ትልቅ ፡ ነህ
አንት ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፭x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists