Kishore Kumar Hits

Yohanes John Girma - Des Yemilehen Sitota lyrics

Artist: Yohanes John Girma

album: Erste Neh, Vol. 1


ደስ ፡ የሚልህን ፡ ስጦታ
በእጄ ፡ ያለኝን ፡ ጌታ
ራሴን ፡ ላድርግ ፡ መስዕዋትህ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ የምሰጥህ
ኑሮህን ፡ ጨርሰህ ፡ በእኔ ፡ ኑር
ካሰብከው ፡ የሚቀርህ ፡ አይኑር (፪x)
በአንተ ፡ መኖር ፡ ያሰብከውን ፡ መኖር
ኑሮህን ፡ መኖር ፡ መርጫለሁ
ብኖር ፡ ለአንተ
ብሞትም ፡ ለአንተ
ከፈቃድህ ፡ ስር ፡ ይሁን ፡ መቃብሬ
ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ኑሮ/ሕይወት ፡ አይታየኝም ፡ እኔ (፪x)
በላይ ፡ ያለው ፡ ፈቅድህ
በምድር ፡ በእኔ ፡ እንዲሆን
ይኸው ፡ ራሴን ፡ አምጥቻለሁ
ለአንተ ፡ እንዲሆን ፡ ሰጥቻለሁ
ለክብርህ ፡ መገለጫ ፡ ዕቃ
የወደድከውን ፡ ማድረጊያ (፪x)
እንደ ፡ ወትሮው ፡ በሥጋዬ
ከብሮ ፡ ሳየው ፡ ውድ ፡ ጌታዬ
ልጁን ፡ በእኔ ፡ መልክ ፡ ገልጦት
ያሰበውም ፡ ሰምሮለት
ደስታዬ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ ይሞላል
መሻቴ ፡ ፍጻሜን ፡ ያገኛል (፪x)
በአንተ ፡ መኖር ፡ ያሰብከው ፡ መኖር
ኑሮህን ፡ መኖር ፡ መርጫለሁ
ብኖር ፡ ለአንተ
ብሞትም ፡ ለአንተ
ከፈቃድህ ፡ ስር ፡ ይሁን ፡ መቃብሬ
ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ኑሮ/ሕይወት ፡ አይታየኝም ፡ እኔ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists