Kishore Kumar Hits

Yohanes John Girma - Erste Neh lyrics

Artist: Yohanes John Girma

album: Erste Neh, Vol. 1


አንተ ፡ ላወቁብህ ፡ ክብር ፡ ነህ
የማዕረግ ፡ መጐናፀፊያ
የሃዘኑ ፡ ዘመን ፡ ማስረሻ
ከማይነጥፍ ፡ ሰላም ፡ መድረሻ
በዕረፍት ፡ ወንዝ ፡ ዳር ፡ ይተከላል
ያገኘህ ፡ ከምንጭ ፡ ዳር ፡ ይኖራል
ዕርዳታው ፡ ከሰማይ ፡ ደጅ
ይወርዳል ፡ የእግዚአብሔር
ዕርዳታው ፡ ከሰማይ ፡ ደጅ
ይወርዳል ፡ የአምላኩ ፡ እጅ
እርስቴ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ ምርጫ
ነፍሴ ፡ አፀደቀህ ፡ የፈቃዴ ፡ ብልጫ
ሁሉንም ፡ ንቄያለሁ ፡ ክብር ፡ በፊቴ ፡ አጣ
ሁሉን ፡ ጥሎ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ ፡ መጣ
ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ
ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ማይገኝ
ቢተካስ ፡ በሌላ ፡ ማያሰኝ
መኖሪያህ ፡ በብርሃናት ፡ ውስጥ
ውበት ፡ ነህ ፡ ለርስትህ ፡ ጌጥ
ለዘለዓለም ፡ ትኖራለህ
ማያረጁ ፡ ዓመታት ፡ ይዘህ
ለሁሌ ፡ ነህ ፡ የነፍሴ፡ ምርጫ
ከአዕላፋት ፡ አግኝተህ ፡ ብልጫ
ለሁሌ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ምርጫ
ከአዕላፋት ፡ አግኝተህ ፡ ብልጫ
እርስቴ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ ምርጫ
ነፍሴ ፡ አፀደቀህ ፡ የፈቃዴ ፡ ብልጫ
ሁሉንም ፡ ንቄያለሁ ፡ ክብር ፡ በፊቴ ፡ አጣ
ሁሉን ፡ ጥሎ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ ፡ መጣ
ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ
ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ
ለሰማይ ፡ ዉበትን ፡ የሰጠህ
ለምድር ፡ ዳርቻን ፡ ያበጀህ
እኔን ፡ በአምሳልህ ፡ መፍጠርህ
የከበርሁ ፡ አርገህ ፡ ማየትህ
ልቤ ፡ በመደነቅ ፡ ተሞላ
ክብሬ ፡ ሊያዜምልህ ፡ ተነሳ
ከልብ ፡ የሚፈልቅ ፡ ምሥጋና
መስዋዕቴ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይግባ
ከልብ ፡ የሚፈልቅ ፡ ምሥጋና
መስዋዕቴ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይግባ
እርስቴ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ ምርጫ
ነፍሴ ፡ አፀደቀህ ፡ የፈቃዴ ፡ ብልጫ
ሁሉንም ፡ ንቄያለሁ ፡ ክብር ፡ በፊቴ ፡ አጣ
ሁሉን ፡ ጥሎ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ ፡ መጣ
ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ
ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists