Kishore Kumar Hits

Bethelhem Tezera - Nu Enawra Silegziabher lyrics

Artist: Bethelhem Tezera

album: Fikir Tetsafe, Vol. 4


ዝም ማለት እዳ ነው ለኔ አይሆንም
የምለው ብዙ አለኝ ለእግዚአብሔሬማ
ጮክ ብዬ ልዘምር ድምፄን ላሰማ
ለስሙ እቀኛለሁ ለሱ እቀኛለሁ አዲስ ቅኔ
ተራሮች ይሰግዳሉ ወንዞች ይዘላሉ እንኳን እኔ
ለጌታ እቀኛለሁ ለሱ እቀኛለሁ አዲስ ቅኔ
አውዓፍ ያዜማሉ ወንዞች ይዘላሉ እንኳን እኔ
ነፃ ወጥቻለሁ ተሰብሮ ቀንበሬ
ፍቅሬን እገልፃለሁ ክብሬን ሰብሬ
ስቦኛል ከትፉ የምህረቱን ገመድ
እንደ እግዚአብሔር የለም በእኔ የሚወደድ
ምን እላለው እንዴት ዝም እላለሁ
አቤት አቤት አቤት አቤት ቸርነትህ
ሲያድለኝ እግሩን ልነካ
አጠብኩት በሺቶ በእንባ
ለኢየሱስ ለልብ ወዳጄ
ልጨምር አልችል ብዬ እንጂ
መጣ ከሰፈሬ ሊፈታኝ ከእስሬ
ነካኝ በፍቅሩ ልሁን ምስክሩ
ልቤን ሳብር አረገው የምሰግድበት መቅደስ ለእግዚአብሔር እንዳጥር በእውነት በመንፈስ
ምን እላለው እንዴት ዝም እላለሁ
አቤት አቤት አቤት አቤት ቸርነትህ
ባለቅኔ አደረገኝ ባለዜማ
ፍቅሩ ልቤን እየቃኘ እንደ በገና
በሉ እናውራ ስለ እግዚአብሔር ኑ እናውራ ታምራት ነው በየዕለቱ የእሱ ስራ
ፍቅሬን የምገልፅበት ልብህን መክፈቻ
መቼም አላገኝም አንተን መርቻ
ክበር ንገስ ልበል ብቻ የልቤ ነህ ልበል ብቻ
ምሕረትህን መገመቻ ቃልም የለኝ አቻ
ክበር ንገስ ልበል ብቻ የልቤ ነህ ልበል ብቻ
ውለታህን መገመቻ ቃል የለኝም አቻ
ምን እላለው እንዴት ዝም እላለሁ
አቤት አቤት አቤት አቤት ቸርነትህ
አምልኮ የሚገባው በዙፋኑ ላይ ያለው
ችዬ እንዴት ዝም እላለው እስትንፋሴ እያለ
ዝማሬ የሚገባው በዙፋኑ ላይ ያለው
ችዬ እንዴት ዝም እላለው እስትንፋሴ እያለ
እልልታ የሚገባው በዙፋኑ ላይ ያለው
ችዬ እንዴት ዝም እላለው እስትንፋሴ እያለ
ዝማሬ የሚገባው በዙፋኑ ላይ ያለው
ችዬ እንዴት ዝም እላለው እስትንፋሴ እያለ
አምልኮ የሚገባው በዙፋኑ ላይ ያለው
ችዬ እንዴት ዝም እላለው እስትንፋሴ እያለ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists