Kishore Kumar Hits

Kalkidan Lily Tilahun - Gena Sayikefel Bahiru lyrics

Artist: Kalkidan Lily Tilahun

album: Eyulign


ሁኔታ መጣ እና ጠየቀኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አለኝ
ነገሩ መጣ እና ጠየቀኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አለኝ
ከፍታው መጣ እና ጠየቀኝ
ዛሬም ታመልኪያለሽ ወይ አለኝ
አዎ አመልካለው ከፍ አረገዋለው
አዎ አመልካለው እባርከዋለው
አዎ አመልካለው ከፍ አረገዋለው
ከፍ አረገዋለው (፬×)

በባዶ እንዳመሰግንህ አምላኬ እድል ሰተኅኛል
ላሳይህ እንዴት እንደማምንህ በባዶ እያመሰገንኩ
በባዶ እንዳመሰግን አንተ እኮ እድል ሰተኅኛል
ላሳይህ እንዴት እንደማምንህ በባዶ እያመሰገንኩ
ተመስገን ተመስገንልኝ (፬×)
ተመስገንልኝ (፬×)

እኔ ዝም ብዬ አላፌዝም ነገር ነገሩን አላይም
ገጣጥዬው እመጣለሁ እምላኬን በጩኅት አመልከዋለው
እኔ ዝም ብዬ አላፌዝም ነገር ነገሩን አላይም
ገነጣጥዬው እወጣለሁ እምላኬን በጩኅት አመልከዋለው
ተመስገን ተመስገንልኝ (፬×)
ተመስገንልኝ (፬×)

ገና ሲያይህ ተከፈለ ባህሩ
ሳይሳካ ነገሩ (፪×)
ገና ሲያይህ ተከፈለ ባህር
ሳይሳካ ነገር (፪×)
እስኪ ላንሳው ከበሮውን ላመስግነው እግዚአብሔርን (፪×)
እስኪ ላንሳ ከበሮዬን ላመስግነው እግዚአብሔርን (፪×)
ተመስገን ተመስገንልኝ (፬×)
ተመስገንልኝ (፬×)
ዝም አልልም አመሰግናለው
ለጌታዬ ክብር ሰጣለው
የጠላቴን ንዝነዛ እምቢ ብዬ
ላመስግንስ ላክበርህ ጌታዬ
ዝም አልልም አመሰግናለው
ለጌታዬ ክብር ሰጣለው
የጠላቴን ንዝነዛ እምቢ ብዬ
ላመስግንስ ላክበርህ ጌታዬ
አመሰግናለው (፬×)
ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ
ክፉ ሁሉ ለጥሩ እንዲለወጥ
ይህንንም ጨምሬ አውቃለው
ስለዚህም አመሰግናለው
አመሰግናለው (፯×)

እስከ ዛሬ ይህንን አውቃለው
እግዚአብሔር መልካም አምላክ ነው
በእግዚአብሔር ላይ ጠላቴ ቢዋሽም
ከማመስገን እኔ ዝም አልልም
አመሰግናለው (፰×)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists