Kishore Kumar Hits

Tamirat Haile - ሰምቶ የሚመልስ lyrics

Artist: Tamirat Haile

album: ሠላም ኢየሱስ ነዉ!


ምድር ለሰው ልጆች ተሰጥታለች አልፋ ፣ ተሰጥታለች አልፋ
ሁሉም በየሙያው ይላል ቀና ደፋ ፣ ይላል ቀና ደፋ
ከዚህ ወዲያ ይባል ከዛ በመለስ ፣ ከዚያ በመለስ
ቅዱሱ ይቀደስ እርኩሱም ይርከስ ፣ እርኩሱም ይርከስ
አይቶ ስምቶ የለየ ፣ ነፃነት አለዉ
እንስበከው እንጂ ፣ ጡንቻ እናሳየው
ያሻውን ይከተል ፣ ሰው እንደገባው
ሰይፋችን ይመለስ ፣ ወደ ሠገባው
ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ
(ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ)
ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን
(ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን)

ምድር ተባርካለች በሃይማኖት ብዛት ፣ በሃይማኖት ብዛት
ህማሟ ባሠ እንጂ ፣ አንዱም አልፈወሳት ፣ አንዱም አልፈወሳት
ምድር ተባርካለች በሃይማኖት ሃብት ፣ በሃይማኖት ሃብት
እንትን እና እንትን እንትን በሚሉት ፣ እንትን በሚሉት
አሁንም ይፈልቃል ፣ በየቀበሌው
እናትና አባት አያት የሌለው
አንዱ ካላዳነ ፣ አያድንም ሺሁ
ወገኔ ተመለስ ፣ ይቅርብህ እልሁ
ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ
(ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ)
ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን
(ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን)

በስራ ይገለጥ የያዝነው እምነት ፣ የያዝነው እምነት
ሙታንም ይነሱ ይወጡ አጋንንት ፣ ይወጡ አጋንንት
ዳንኩኝ ተፈወስኩኝ ብለው ይመስክሩ ፣ ብለው ይመስክሩ
የሃይማኖት ፋይዳ ይህ ነው ቁም- ነገሩ ፣ ይህ ነው ቁም-ነገሩ
የሚያድን እምነት ፣ የሚያደርስ ሰማይ
ከሌለው ሰው አርፎ ፣ ሠርቶ አይበላም ወይ
በሰላም አንደር ፣ አይረበሽ ሠፈር
ድንበር አትለፉ ፣ ተዉ አንደፋፈር
ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ
(ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ)
ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን
(ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን)

ደርሶ ስም ለማጥፋት ወሬ አሉባልታ ፣ ወሬ አሉባልታ
ጭራሽ ይባስ ብሎ ባስክሬን ጨዋታ ፣ ባስክሬን ጨዋታ
ትዳርን አፋቶ ልጅ ከናት ነጥሎ ፣ ልጅ ከእናት ነጥሎ
ከቀዬ ከሠፈር ከማህበር አግልሎ ፣ ከማህበር አግልሎ
ከገነት ሊገባ እንዲያው መታሰቡ ፣ ቁርጥህን እወቀው አትደርስ ካጠገቡ
አሳደው እሠራው ግደልልኝ ያለ ፣ ዲያቢሎስ ነው እንጂ እግዚያብሔር አይደለ
ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ
(ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ)
ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን
(ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን)

የኔ ይበልጣል ቢሉ ምንም ክፋት የለው ፣ ምንም ክፋት የለው
እኛ ማንስማማው ዛቻ ሲጀመር ነው ፣ ዛቻ ሲጀመር ነው
እግዚያብሔር ትልቅ ነው ለሁሉም ሚበቃ ፣ ለሁሉም ሚበቃ
ምስክር ነው እንጂ አያሻው ጠባቃ ፣ አያሻው ጠባቃ
እናንተ የአምላክ ልጆች ፣ ከቶ አትታወኩ
ሁሉም በየቋንቋው ፣ ይጩህ ወዳምላኩ
የሁሉም ማንነት ፣ በተግባር ይታያል
የኤልያስ አምላክ ፣ በእሳት ይለያል
ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ
(ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ)
ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን
(ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists