Kishore Kumar Hits

Tamirat Haile - ሰላም ኢየሱስ ነው lyrics

Artist: Tamirat Haile

album: ሠላም ኢየሱስ ነዉ!


አዝ፦ ሰላም ሰላም ኢየሱስ ነው
ደጁ ሳይከፈት ግድግዳው ሳይፈርስ
የሰላሙ ጌታ ገባ ኢየሱስ
ለተጨነቁቱ ግራ ለገባቸው
ሰላም ለእናንተ ይሁን ብሎ አሳረፋቸው
አዝ፦ ሰላም ሰላም ኢየሱስ ነው
በጠመንጃ አፈ ሙዝ ወይ በእርቅ ድርድር
የተገኘ ሰላም አላየንም በምድር
ከዚህ የተቋጠረ ከዚያ ጋር ተፈታ
ስላልቀደመ ነው የሰላሙ ጌታ
አዝ፦ ሰላም ሰላም ኢየሱስ ነው
የሃገር መሪዎች ክብር ሥልጣናቹህ
የውክልና ነው ወዶ የሰጣችሁ
ሞኝነት ቢመስልም ጌታን ተቀበሉ
ህዝቡን እንድመራ እኔን ምራ በሉ
አዝ፦ ሰላም ሰላም ኢየሱስ ነው
አውራጃው ወረዳው ቀበሌም መንደሩ
ንግዱም ሃይማኖቱም እድር ማህበሩም
ምድር እንዲፈወስ አየር እንዲጠራ
ሁሉም እጁን ያንሳ ኢየሱስን ይጥራ
አዝ፦ ሰላም ሰላም ኢየሱስ ነው
ምሁር ነህ ተማሪ ሃኪም ገበሬዉ
ኢየሱስ ያድናል ጥሪው ላንተም ነው
የትዳርህ ኪዳን ጐጆህ አይፍረስ
የሰላሙ ሉዑል በቤትህ ይንገሥ
አዝ፦ ሰላም ሰላም ኢየሱስ ነው
መጠጥና ዘፈን ጐበዝና ቆንጆው
አቃወሰህ ጤናህ አፈረሰ ጐጆው
ደግሞ የእሳት ፍርድ አለ ከዚህ የባሰዉ
የአምላክ ጥሪ ሰምቶ ላልተመለሰው
አዝ፦ ሰላም ሰላም ኢየሱስ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists