Kishore Kumar Hits

Tamirat Haile - ድረስልኝ lyrics

Artist: Tamirat Haile

album: ሠላም ኢየሱስ ነዉ!


በጉድለት ፡ ነው ፡ የምመላለሰው
የሞላሁኝ ፡ እመስላለሁ ፡ ለሰው
ያውቀው ፡ የለ ፡ ጌታ ፡ ውስጤን ፡ ዘልቆ
ግብዝነት ፡ የትም ፡ አይሄድ ፡ ርቆ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
ቀባብቼ ፡ ውጬዬን ፡ አሳምሬ
ማስመሰሉን ፡ እንጃ ፡ ከየት ፡ ተምሬ
መቅረብ ፡ ትቼ ፡ ሆኜ ፡ እራሴን
አዘገየው ፡ መጐብኘት ፡ ፈውሴን
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
አውቀዋለሁ ፡ ባሕረ ፡ ገሊላ
አይካድም ፡ አሳም ፡ እንደሞላ
የማጥመድስ ፡ ልምድ ፡ መች ፡ አጥቼ
ልሂድ ፡ እንጂ ፡ ዋናውን ፡ ረስቼ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ
ለረድኤት ፡ እጄን ፡ አነሳለሁ
ኧረ ፡ ወዴት ፡ ወዴት ፡ ሊኬድ ፡ ከቶ
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ ትቶ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
ይህ ፡ አየነ ፡ ስውር ፡ ደግመህ ፡ ብትዳስሰው
አጥርቶ ፡ አየ ፡ ለይቶ ፡ ዛፍ ፡ ከሰው
ደግመህ ፡ ዳሰኝ ፡ እኔንም ፡ ጌታዬ
እልፍ ፡ ይበል ፡ ይስፋ ፡ እይታዬ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
አንተ ፡ ምንጭ ፡ ሆይ ፡ ፍለቅልን ፡ እባክህ
ጠጥተንህ ፡ እንድንባረክ
ለልጆችህ ፡ ላለን ፡ በበረሃ
ፍሰስልን ፡ አንተ ፡ የሕይወት ፡ ውሃ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ
ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ድረስልኝ ፡ ምርኮዬን ፡ መልስልኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists