Kishore Kumar Hits

Tamirat Haile - እስከ ዛሬ የጠበቀኝ lyrics

Artist: Tamirat Haile

album: ሠላም ኢየሱስ ነዉ!


እስከዛሬ ፡ የጠበቀኝ ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ ያለቀቀኝ
የክርስትናን ፡ ቀጭን ፡ መንገድ ፡ የሕይወትን ፡ ውጣ ፡ ውረድ
ባይበዛልኝ ፡ የእርሱ ፡ ፀጋ ፡ አንዷም ፡ ሌሊት ፡ አትነጋ
ዛሬም ፡ ቆምኩኝ ፡ በዚህ ፡ ቦታ ፡ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ባይበዛልኝ ፡ የእርሱ ፡ ፀጋ ፡ አንዷም ፡ ሌሊት ፡ አትነጋ
ዛሬም ፡ ቆምኩኝ ፡ በዚህ ፡ ቦታ ፡ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና
እንደጠላት ፡ አሳብ ፡ ቢሆን ፡ ከሆነልኝ ፡ አንዱም ፡ አይሆን
ታሪክ ፡ ቢያብብ ፡ ሕይወት ፡ ቢያምር ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ በእርሱ ፡ ተዐምር
ከእያንዳንዷ ፡ እስትንፋስ ፡ ስጦታ ፡ ናት ፡ የኢየሱስ
ከፈቀደ ፡ ይሁን ፡ ካለ ፡ አይሆንም ፡ የሚል ፡ ማን ፡ አለ
ከእያንዳንዷ ፡ እስትንፋስ ፡ ስጦታ ፡ ናት ፡ የኢየሱስ
ከፈቀደ ፡ ይሁን ፡ ካለ ፡ አይሆንም ፡ የሚል ፡ ማን ፡ አለ
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና
አንተ ፡ . ጥላቴ ፡ ቀናተኛ ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አትተኛ
እንደተራበ ፡ አንበሳ ፡ ዙሪያዬን ፡ ብትዞር ፡ እያገሳህ
ልትውጠኝ ፡ ብትመኘኝ ፡ ሲያምርህ ፡ ይቅር ፡ አታገኘኝ
በስሙ ፡ አጥር ፡ በደሙ ፡ እሳት ፡ ከልሎኛል ፡ የእኔ ፡ አባት
ልትውጠኝ ፡ ብትመኘኝ ፡ ሲያምርህ ፡ ይቅር ፡ አታገኘኝ
በስሙ ፡ አጥር ፡ በደሙ ፡ እሳት ፡ ከልሎኛል ፡ የእኔ ፡ አባት
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና
ያንን ፡ ዘንዶ ፡ እባቡን ፡ የወጋኸው ፡ ወገቡን
ራስ ፡ እራሱን ፡ ያስረገጥከኝ ፡ ስንቱን ፡ ነገር ፡ ያስመለጥከኝ
ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ጋሻዬ ፡ በክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሺያዬ
መቆሚያዬ ፡ ነህ ፡ አለቴ ፡ ላመስግንህ ፡ በአንደበቴ
ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ጋሻዬ ፡ በክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሺያዬ
መቆሚያዬ ፡ ነህ ፡ አለቴ ፡ ላመስግንህ ፡ በአንደበቴ
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያbልቅምና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists