Kishore Kumar Hits

Tamirat Haile - ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ lyrics

Artist: Tamirat Haile

album: ሠላም ኢየሱስ ነዉ!


አቀበት ፡ ሜዳ ፡ ገደላ ፡ ገደል
የታለፈበት ፡ የሚረሳ ፡ አይደል
ነዳፊው ፡ እባብ ፡ ነካሹ ፡ አውሬ
ስንት ፡ አስረገጠኝ ፡ በዚህ ፡ በእግሬ
የሠማይ ፡ አምላክ ፡ አቤት ፡ ምህረቱ
ማድረግ ፡ ይችላል፡ ደካማን ፡ ብርቱ
በእርሱ ፡ ሆናችሁ ፡ ያያችሁ ፡ ብዙ
በዕልልታ ፡ ሆታ ፡ ምሥጋናን ፡ አብዙ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ
መካሪ ፡ ወንድም ፡ ወላጅ ፡ አባቴ
የሆነልኝ ፡ ሁሉ ፡ በሁሉ
ቆርቁሮኝ ፡ አያውቅ ፡ ጠባይ ፡ አመሉ
ጣቱን ፡ በመያዝ ፡ ዳዴ ፡ ተምሬ
ቆሜ ፡ ለመሄድ ፡ ሆኖልኝ ፡ ዛሬ
የጥንቱ ፡ አምላክ ፡ የልጅነቴ
ዛሬም ፡ ላክብረው ፡ በአንደበቴ
ይሄ ፡ ክፉ ፡ ዓለም ፡ ምኑ ፡ ይመቻል
በሥጋ ፡ በደም ፡ የትኛው ፡ ሲቻል
በየማለዳው ፡ አዲስ ፡ በሆነው
በምህረቱ ፡ ነው ፡ ያልጠፋነው
እንደ ፡ እኔ ፡ ቢሆን ፡ እንደድካሜ
ዛሬም ፡ በፊቱ ፡ ባልታየሁ ፡ ቆሜ
በዓይኔ ፡ እያየሁት ፡ አለፈ ፡ ስንቱ
የያዘኝ ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብርቱ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ
መካሪ ፡ ወንድም ፡ ወላጅ ፡ አባቴ
የሆነልኝ ፡ ሁሉ ፡ በሁሉ
ቆርቁሮኝ ፡ አያውቅ ፡ ጠባይ ፡ አመሉ
ጣቱን ፡ በመያዝ ፡ ዳዴ ፡ ተምሬ
ቆሜ ፡ ለመሄድ ፡ ሆኖልኝ ፡ ዛሬ
የጥንቱ ፡ አምላክ ፡ የልጅነቴ
ዛሬም ፡ ላክብረው ፡ በአንደበቴ
ይህን ፡ ዮርዳኖስን ፡ ስሻገረው
ደረቅ ፡ በትር ፡ ነው ፡ በእጄ ፡ የነበረው
ዛሬ ፡ ግን ፡ ይሄው ፡ ዓለመለኝ
በተዓምራቱ ፡ እያስገረመኝ
ሕይወት ፡ ዥንጉርጉር ፡ ቀለሙ ፡ ብዙ
መች ፡ ቀላል ፡ ሆነ ፡ ጓዙ ፡ መዘዙ
የሰበሰበኝ ፡ የያዘኝ ፡ ጌታ
ስሙ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ በዕልልታ ፡ ሆታ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ
መካሪ ፡ ወንድም ፡ ወላጅ ፡ አባቴ
የሆነልኝ ፡ ሁሉ ፡ በሁሉ
ቆርቁሮኝ ፡ አያውቅ ፡ ጠባይ ፡ አመሉ
ጣቱን ፡ በመያዝ ፡ ዳዴ ፡ ተምሬ
ቆሜ ፡ ለመሄድ ፡ ሆኖልኝ ፡ ዛሬ
የጥንቱ ፡ አምላክ ፡ የልጅነቴ
ዛሬም ፡ ላክብረው ፡ በአንደበቴ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists