Kishore Kumar Hits

Tamirat Haile - ተራራ የሚናድለት lyrics

Artist: Tamirat Haile

album: እግዚአብሔር አዋቂ ነው


ቃሉ ሲያስተምረን ፣ መንፈሱ ሲያፅናናን
አቻምናን አለፍን ተሻገርን አምናን
ጠላት ቢቃወመን ፣ እጅግ ተገዳድሮ
ጌታ ተዋግቶልን ደረስን ዘንድሮ ፣ ደረስን ዘንድሮ
ተራራ የሚናድለት ፣ ጨለማ ሚገፈፍለት
ነፋሳት የሚገዙለት ፣ ወጀቡ ሚታዘዝለት
እየሱስ እየሱስ ክብር ይሁንልህ
መጻተኞች ብንሆን ፣ ምድር ያልተገባን
ምንም አልጎደለን ለኛ ከሚረባን
ወላጅ እንደሌለው ፣ ልጅ አላደረገን
የሁላችን አባት እግዚአብሔር ይመስገን ፣ እግዚአብሔር ይመስገን
ተራራ የሚናድለት ፣ ጨለማ ሚገፈፍለት
ነፋሳት የሚገዙለት ፣ ወጀቡ ሚታዘዝለት
እየሱስ እየሱስ ክብር ይሁንልህ
ጉንድሹ ቢመጣ፣ አካሉ ተሟልቶ
አውሩ በወጣ ሄደ አይኑ ተከፍቶ
ሙታን ተነስተዋል ፣ የተራቡም በሉ
እጁን ከዘረጋ ይደርሳል ለሁሉ ፣ ይደርሳል ለሁሉ
ተራራ የሚናድለት ፣ ጨለማ ሚገፈፍለት
ነፋሳት የሚገዙለት ፣ ወጀቡ ሚታዘዝለት
እየሱስ እየሱስ ክብር ይሁንልህ
ህዝቡ እንደሆነ አይቀር ፣ ተስፋውን መውረሱ
ፈርኦን ለምን ነው ሃይሉን መጨረሱ
ባህር ተከፈለ ፣ በድል ተሻገሩ
እንዴ እስከ ዘላለም ተሰብሯል ቀንበሩ ፣ ተሰብሯል ቀንበሩ
ተራራ የሚናድለት ፣ ጨለማ ሚገፈፍለት
ነፋሳት የሚገዙለት ፣ ወጀቡ ሚታዘዝለት
እየሱስ እየሱስ ክብር ይሁንለት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists