Kishore Kumar Hits

Tamirat Haile - እግዚአብሔር አዋቂ ነው lyrics

Artist: Tamirat Haile

album: እግዚአብሔር አዋቂ ነው


እግዚአብሔር አዋቂ ነው ፣ አዋቂ ነው ፣ አዋቂ ነው
ስራችንን ይመዝናል ፣ ዋጋችንን ይተምናል
ከፋኝ ብለን አናጉረምርም ስለሁሉ እናመስግነው
ደላኝ ብለን አንታበይ እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ቃልን ለመናገር አንደበት ቸኩሎ
ሲያነሳ ሲጥል ባልዋሉበት ውሎ
ለምን እናፍራለን በተናገርንበት
እርሱ ያደላድላል ሁሉንም ተውለት
ሃሰት ሲሆን እውነት ያልነው
ጸድቆ ሲገኝ የኮንነው
አንተ ያልነው ሲሆን አንቱ
ለእኛ ሚቀረን ትዝብቱ
እግዚአብሔር አዋቂ ነው ፣ አዋቂ ነው ፣ አዋቂ ነው
ስራችንን ይመዝናል ዋጋችንን ይተምናል
ከፋኝ ብለን አናጉረምርም ስለሁሉ እናመስግነው
ደላኝ ብለን አንታበይ እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ፍሬ የሌለባት የደረቀች ዛፍ
እያሉ ገረፏት ስታገድም ስታልፍ
ኋላም ሰባት ወልዳ ምስኪን መካኒቱ
የተባለው ሁሉ መና ሲሆን ከንቱ
ልዑል አምላክ ከፍ ሲያደርጋት
ቢንጠራሩ ላይደርሱባት
አዋቂ ነው እግዚአብሔር
ብላ ተቀኘች በመዝሙር
እግዚአብሔር አዋቂ ነው ፣ አዋቂ ነው ፣ አዋቂ ነው
ስራችንን ይመዝናል ዋጋችንን ይተምናል
ከፋኝ ብለን አናጉረምርም ስለሁሉ እናመስግነው
ደላኝ ብለን አንታበይ እግዚአብሔር አዋቂ ነው

ፈተና በዝቶብን ብናዝን ብንከፋ
ቢወሳሰብብን ውሉ እስከሚጠፋ
ሚስጥሩ የአምላክ ነው ሁሉም ነገር በእጁ
የተገለጠው ግን ለእኛ ለልጆቹ
ሁሉን ሲያደርግ የለን በጐ
ሲያበጃጀው ውብ አድርጐ
እናያለን የእርሱን ማዳን
እንድንጸና ጌታ ይርዳን
እግዚአብሔር አዋቂ ነው ፣ አዋቂ ነው ፣ አዋቂ ነው
ስራችንን ይመዝናል ዋጋችንን ይተምናል
ከፋኝ ብለን አናጉረምርም ስለሁሉ እናመስግነው
ደላኝ ብለን አንታበይ እግዚአብሔር አዋቂ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists