Kishore Kumar Hits

Tamirat Haile - ተራራው ዝቅ ይበል lyrics

Artist: Tamirat Haile

album: እግዚአብሔር አዋቂ ነው


ተራራው ዝቅ ይበል ፣ ሸለቆው ከፍ ይበል
ስርጓጎጡም ሜዳ ይሁን ፣ ጠማማውም ይቅና
ስጋ ለባሽ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን እንዲያይ
የአዋጅ ነጋሪው ድምጽ ሳይታክት ይጮሃል
መንገድን በበረሃ አስተካክሉለት ይላል
ልባችንን አናደንድን አይልበስ ጆሮ ዳባ
በሮችን ክፈቱለት የክብር ንጉሥ ይግባ
ተራራው ዝቅ ይበል ፣ ሸለቆው ከፍ ይበል
ስርጓጎጡም ሜዳ ይሁን ፣ ጠማማውም ይቅና
ስጋ ለባሽ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን እንዲያይ
ማዳኑ እንዳይገለጥ ክንዱ እንዳይዘረጋ
ብዙ እንቅፋት አለ እኔና እናንተ ጋር
የድካሙ ሸለቆ የትዕቢት ኮረብታ
ከልክሎት የለም ወይ ክብሩን እንዳይገልጥ ጌታ
ተራራው ዝቅ ይበል ፣ ሸለቆው ከፍ ይበል
ስርጓጎጡም ሜዳ ይሁን ፣ ጠማማውም ይቅና
ስጋ ለባሽ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን እንዲያይ
ጆሮዎቹ ከመስማት መቼም አልደነቆሩም
ከማዳን ከመፈወስ እጆቹስ መቼ አጠሩ
እንደ ግድግዳ ሆኖ ኀጢአት ነው የለየን
የተገባልን ተስፋ በሙላት መቼ አየን
ተራራው ዝቅ ይበል ፣ ሸለቆው ከፍ ይበል
ስርጓጎጡም ሜዳ ይሁን ፣ ጠማማውም ይቅና
ስጋ ለባሽ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን እንዲያይ
ጠላትን አሳልፎ በእጃችን ሊሰጠን
መንፈሱን ሊያፈስልን ሊሰራን ሊለውጠን
የሰራዊቱ ጌታ ያልፋል በሰፈራችን
በንሰሃ እንውደቅ በደሙ ይንፃ ጓዳችን
ተራራው ዝቅ ይበል ፣ ሸለቆው ከፍ ይበል
ስርጓጎጡም ሜዳ ይሁን ፣ ጠማማውም ይቅና
ስጋ ለባሽ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን እንዲያይ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists