Kishore Kumar Hits

Tamirat Haile - እግዚአብሔር ይባርክህ lyrics

Artist: Tamirat Haile

album: እግዚአብሔር አዋቂ ነው


በአንድነት አስሮ በፍቅር ባርኮ
ይስብስብልህ ምርኮ በምርኮ
ብዛ ተባዛ የአባቴ መንጋ
የሚነሳብህ ወገቡ ይወጋ
እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
የጽድቅን ኑሮ የቅድስናን
እያበዛልህ ጸሎት ጽሞናን
የቃሉን ረሃብ የአምልኮን ጥማት
ያትረፍርፍልህ ቅባት በቅባት
እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
ሽማግሌዎች ከአደባባይ
ህጽናት ልጆች ከሜዳው ላይ
የአዝመራው ማሳ የአምልኮ መድረክ
ሁሉም ይለምልም ሁሉም ይባረክ
እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
የግብጽ ቁስል ደዌ ቸነፈር
ጭንገፋና ሞት አንተን አይድፈር
ቀሳፊው መልአክ ቤትህ አይግባ
ጉበን መቃንህ በደሙ ይቀባ
እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
ተምች አይውረር ደግሞም ኩብኩባ
የአየር ንብረትህ እንዳይዛባ
ወንዝ አፈርህን ጌታ ይባርክልህ
ቁርባን መስዋዕትህን ያለምልምልህ
እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists