Kishore Kumar Hits

Selam Desta - Beki New lyrics

Artist: Selam Desta

album: Alderaderem


በጣም የከበረ እጅግ ያየለ
ከወርቅ እንቁ ይልቅ የተሻለ
በፍፁም ድርድር አብ የማያውቅበትን
አንድያ ልጁን ሰጠ ኢየሱስን
በጣም የከበረ እጅግ ያየለ
ከወርቅ እንቁ ይልቅ የተሻለ
በፍፁም ድርድር አብ የማያውቅበትን
ክንዱን ሰጠ ኢየሱስን
በቂ ነው ከበቂም በላይ (፫x)
ለሰማይ ቢሉ ለምድሩም ሲሳይ
በቂ ነው ከበቂም በላይ (፫x)
ለሰማይ ቢሉ ለምድሩም ሲሳይ
ስቀበለው ያኔ እንደግል አዳኝ
መዘገበው ስሜን በላይኛው ሰማይ
የቅዱሳን ተስፋ በረከቴ ሆኖኛል
ቀረኝ የምለው የለም አብ ጨርሶ ባርኮኛል
ስቀበለው ያኔ እንደግል አዳኝ
መዘገበው ስሜን በላይኛው ሰማይ
የቅዱሳን ተስፋ ስጦታዬ ሆኖኛል
ቀረኝ የምለው የለም አብ ሁሉንም ሰጥቶኛል
ከዚህ በላይ ባርኮት ምናለ ከዚህ በላይ በላይ
ከዚህ በላይ ደስታስ ምናለ ከዚህ በላይ በላይ
ከዚህ በላይ ሰላም ምናለ ከዚህ በላይ በላይ
አለም የሌላትን አገኘሁ ከላይ ከሰማይ
ዓሣ በምድር ላይ ሕይወት አያምረው
ከባህር እርቆ መኖር አያሰኘው
ሁልግዜ መገኛው አንድ እና አንድ ነው
ከውሀ የወጣ እለት መሞቻው ቅርብ ነው
ዓሣ በየብስ ላይ ሕይወት አያምረው
ከባህር እርቆ መኖር አያሰኘው
ሁልግዜ መገኛው አንድ እና አንድ ነው
ከውሀ የወጣ እለት መሞቻው ቅርብ ነው
የእኔም ያለኢየሱስ ልክ እንዲህ ባዶ ነው
ከመገኛ እርቆ መኖር ኧረ እንዴት ከንቱ ነው
የሕይወት እንጀራ ጠግቤ የሕይወት ውሀ ረክቼ
ከእርሱ ወዴት እሄዳለሁ
መገኛዬ አንድ እና አንድ ነው
በረከቴ ኢየሱስ ብቻ ነው
በቂ ነው ከበቂም በላይ (፫x)
ለሰማይ ቢሉ ለምድሩም ሲሳይ
በቂ ነው ከበቂም በላይ (፫x)
ለሰማይ ቢሉ ለምድሩም ሲሳይ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists