Kishore Kumar Hits

Selam Desta - Beka Dankugne lyrics

Artist: Selam Desta

album: Alderaderem


አንተን እየሰጋሁ እኔን ያመንኩበት
እየጠረጠርኩህ በእኔ እርግጥ የሆንኩበት
ለካ የከንቱነቴ የሞኝነት ዘመን ነው
ዛሬ ግን ነቅቼ እምነቴ ነህ እላለሁ
ለካ የከንቱነቴ የሞኝነት ዘመን ነው
ዛሬ ግን ሲገባኝ ሕይወቴ ነህ እላለው
አንተን እየሰጋሁ እኔን ያመንኩበት
እየጠረጠርኩህ በእኔ እርግጥ የሆንኩበት
ለካ የከንቱነቴ የሞኝነት ዘመን ነው
ዛሬ ግን ሲገባኝ ህይወቴ ነህ እላለሁ
ለካ የከንቱነቴ የሞኝነት ዘመን ነው
ዛሬ ግን ሲገባኝ ማኅተሜ እላለሁ
አንተ እምነቴ ነህ (፭x)
ኢየሱስ ሕይወቴ ነህ
አንተ ተስፋዬ ነህ (፪x)
አንተ ማህተሜ ነህ (፪x)
አንተ ሕይወቴ ነህ
ኢየሱስ እምነቴ ነህ

ባለማወቅ ጠንቅ በልበ ደንዳናነት የጨለምኩ
ይህን ዓለም ለሚገዛ ለክፉ መንፈሥ ባሪያ ነበርኩ
በዘላለም ቁጣ ተጥዬ ከአብ ሕይወት የራቅኩኝ
ገና ከፍጥረቴ ሙት ነበርኩኝ
የማመጣው የዋኖስ ደም አይደለም ያነፃኝ
አብን እንዳየው ጸጋህ ነው የረዳኝ
የማመጣው የበግ ደም አይደለም ያነፃኝ
አብን እንዳምነው ጸጋህ ነው የረዳኝ
በቃ ዳንኩኝ በሥራህ
በቃ ዳንኩኝ በአቅምህ
ለእኔ መዳኛ ነው ጸጋህ
በቃ ዳንኩኝ በሥራህ
በቃ ዳንኩኝ በአንተ አቅም
ለእኔ መዳኛ ነው መሞትህ
ለእኔ መዳኛ ነው ስራህ
ለእኔ መዳኛ ነው ትጋትህ

በደሌን ተሸክመህ ለዓለም እና ለአብ አንዴ ታይተሀል
ፅድቅን አልብሰህ ለዘላለም በቀኙ አኑረሀል
መልከጼዴቄ ባንተ እኔ ዳንኩኝ
ከአቤል ደም ባየለ በደምህ ነፃሁኝ
ከከንቱ እሩጫ ባንተ ታቅቤ
ሞት ላይከጅለኝ መንደር ቀይሬ
በምሕረትህ ብርታት ከጠላት ኮበለልኩ
ከድካሜ ይልቅ ሃይልህንም አመንኩ
ከከንቱ እሩጫ ባንተ ታቅቤ
ሞት ላይከጅለኝ ስፈር ቀይሬ
በምሕረትህ ብርታት ከጠላት አመለጥኩ
ከስራዬ ይልቅ ፀጋህንም አመንኩ
ከድካሜ ይልቅ ሃይልህንም አመንኩ
ከስራዬ ይልቅ ትጋትህንም አመንኩ
በቃ ዳንኩኝ በሥራህ
በቃ ዳንኩኝ በአንተ አቅም
ለእኔ መዳኛ ነው ፀጋህ
በቃ ዳንኩኝ በሥራህ
በቃ ዳንኩኝ በአንተ አቅም
ለእኔ መዳኛ ነው መሞትህ
ለእኔ መዳኛ ነው ስራህ
ለእኔ መዳኛ ነው መሞትህ
ለእኔ መዳኛ ነው ፀጋህ
ለእኔ መዳኛ ነው መሞትህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists