Kishore Kumar Hits

Selam Desta - Kibrehe Yelelebet lyrics

Artist: Selam Desta

album: Alderaderem


ሴም ካም ያፌት ትውልዳቸው (፪×)
በዝቶ ቢታይም ዘር ሀረጋቸው
ሳንበታተን እንዲህ ባለንበት ስማችን ይጠራ
ብለው ቢነሱ በድፍረት ልባቸው ሳይፈራ
መች ተፈፀመ ሀሳባቸው
በመንገድ ቀረ ህልማቸው
ክብርህን ሳይሉ ክብሬን ስላሉ
በመንገድ ትጥቃቸውን አላሉ
መች ተፈፀመ ሀሳባቸው
በመንገድ ቀረ ህልማቸው
ክብርህን ሳይሉ ክብሬን ስላሉ
በመንገድ ትጥቃቸውን አላሉ
አስበኝ እኔን ለክብርህ እንድኖር (፪×)
አስበኝ እኔን ለሀሳብህ እንድቆም
አስበኝ እኔን ለክብርህ እንድኖር (፪×)
አስበኝ እኔን ለሀሳብህ እንድቆም
ክብርህ የሌለበት አይሁን ክብሬ
ማትጠራበት አይሁን መጠሪያዬ
ማትገኝበት አይሁን መገኛዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን መዋያዬ
ክብርህ የሌለበት አይሁን ክብሬ
ማትጠራበት አይሁን መጠሪያዬ
ማትገኝበት አይሁን መገኛዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን ማደሪያዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን መዋያዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን ማደሪያዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን መኖሪያዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን መሞቻዬ
ኦዝያ ዝናው ገነነ ከዳር እስከ ዳር ታወቀ (፪×)
ዝናው በወጣ ልክ ስራውም ደመቀ
ሞገሱን እያየ በአምላክ ላይ ታበየ
ክብሩን እያየ በአምላክ ላይ ታበየ
ለምፅን ጣለ በፊቱ ሞገስን አነሳ ከህይወቱ
አለም የሚያውቀውንም ኦዝያ
እፍረት አለበሰ በቤቱ
ለምፅን ጣለ በፊቱ ሞገስን አነሳ ከህይወቱ
ህዝብ የሚያውቀውንም ኦዝያ
እፍረት አለበሰ በቤቱ
አስበኝ እኔን ለክብርህ እንድኖር (፪×)
አስበኝ እኔን ለሀሳብህ እንድቆም
አስበኝ እኔን ለክብርህ እንድኖር (፪×)
አስበኝ እኔን ለሀሳብህ እንድቆም
ለራስ ትኩረት መሮጥ ለማን በጀ
ልታይ ባይነት ያልደበቀውስ ማን አለ
ኢየሱስን የሸፈነ ዘመን ከኔ ይራቅ
በጥቂቷም ዘመኔ ኢየሱስ ደምቆ ይታይ
ለራስ ትኩረት መሮጥ ለማን በጀ
ልታይ ባይነት ያልደበቀውስ ማን አለ
ኢየሱስን የሸፈነ ህይወት ከኔ ይራቅ
በጥቂቷም ዘመኔ ኢየሱስ ደምቆ ይታይ
ኢየሱስ ደምቆ ይታይ
ኢየሱስ ከፍ ብሎ ይታይ
ኢየሱስ ደምቆ ይታይ
ኢየሱስ ደምቆ ይታይ
ባከበርከኝ ልኩ ልዋረድ
ከፍ ባልኩኝ ቁጥር ዝቅ ልበል
ግብዝነት የሌለ ህይወት በእኔ ይገለጥ
በፊትህ ዘመኔ ይመረጥ
ባከበርከኝ ልኩ ልዋረድ
ከፍ ባልኩኝ ቁጥር ዝቅ ልበል
ግብዝነት የሌለ ህይወት በእኔ ይገለጥ
በፊትህ ህይወቴ ይመረጥ
ለስሜ አልሮጥም ለክብሬ
ለታይታ አልኖርም ደፍሬ
ያንን ይሄንን ለእኔ አልልም
ካልከበርክበት ጋር አልባክንም
ለስሜ አልሮጥም ለክብሬ
ለታይታ አልኖርም ደፍሬ
ያንን ይሄንን ለእኔ አልልም
ካልከበርክበት ጋር አልባክንም
ክብርህ የሌለበት አይሁን ክብሬ
ማትጠራበት አይሁን መጠሪያዬ
ማትገኝበት አይሁን መገኛዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን መዋያዬ
ክብርህ የሌለበት አይሁን ክብሬ
ማትጠራበት አይሁን መጠሪያዬ
ማትገኝበት አይሁን መገኛዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን ማደሪያዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን መዋያዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን ማደሪያዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን መኖሪያዬ
ከእቅፍህ ስር ይሁን መሞቻዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists