Kishore Kumar Hits

Selam Desta - Na Geta Yiwedehal lyrics

Artist: Selam Desta

album: Alderaderem


እርቆ ለጠፋ ድርሻውን ይዞ
ከአባቱ ቤት ኮብልሎ ወደ ምኞት ጉዞ
እጅግ ክፉን ቢያደርግ ቢሆን ተላላ
ነፍሱን አልጠቀመም ከፍቶታል በጣም
እርቆ ለጠፋ ድርሻውን ይዞ
ከአባቱ ቤት ኮብልሎ ወደ ምኞት ጉዞ
እጅግ ክፉን ቢያደርግ ቢሆን ተላላ
ነፍሱን አልጠቀመም ከፍቶታል በጣም
አንድ ቀን ሲመለስ ወደ ልቡ
ሀሳቡን ሰብስቦ ሲቃኝ አባቱን
ይኖር ነበረ በደስታ
አሁን ግን ገብቶታል መሆኑ ጎስቋላ
አንድ ቀን ሲመለስ ወደ ልቡ
ሀሳቡን ሰብስቦ ሲቃኝ አባቱን
ይኖር ነበረ በደስታ
አሁን ግን ገብቶታል መሆኑ ጎስቋላ
እንደ ልጁ ባያየኝ እንኳን ልሁን እንደ ባሪያ
ብሎ ለወሰነ ለቆረጠ ጀግና
ገና ሳይገባ ወደ መንደሩ
አባቱ አቀፈው በፍቅር እጁ
እንደ ልጁ ባያየኝ እንኳን ልሁን እንደ ባሪያ
ብሎ ለወሰነ ለቆረጠ ጀግና
ገና ሳይገባ ወደ መንደሩ
አባቱ አቀፈው ልክ እንደበፊቱ
ና ና ና ጌታ ይወድሀል
ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል
ና ና ና ውዴ ይወድሀል
ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል

ሁሉ እንዲመለስ በንስሀ ወዶ ይታገሳል ጌታ
ዝምታው በኃጥያት አይደለም ማለት በርታ
ቀን እጅግ ሳይከፋ ሳይመጣ የጥፋት ውሀ
መዳን በልጁ ግባ ወደ መርከቡ
ሁሉ እንዲመለስ በንስሀ ወዶ ይታገሳል ጌታ
ዝምታው በኃጥያት አይደለም ማለት በርታ
ቀን እጅግ ሳይከፋ ሳይመጣ የጥፋት ውሀ
አ መዳን በልጁ ግባ ወደ መርከቡ
መርከብ ኢየሱስ ነው ማምለጫ መርከብ
ወጀቡ ቢያልም ፍፁም አትሰጋበት
መርከብ ኢየሱስ ነው ማምለጫ መርከብ
ወጀቡ ቢያልም ፍፁም አትሰጋበት
ና ና ና ጌታ ይወድሀል
ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል
ና ና ና ውዴ ይወድሀል
ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል

ቢጠላ እንጂ ሀጥያትን ኃጥያተኛን ከልቡ ይወዳል
ይሉት የለ ወይ ቀድሞም እርሱ ከአመጸኞች ጋር ይወዳጃል
መሪ አጥተው ለተበተኑ እውነተኛ እረኛ ነው
ይሰበስባል በፍቅር እጁ አቅፎ ያሞቃል በእቅፉ
ቢጠላ እንጂ ሀጥያትን ኃጥያተኛን ከልቡ ይወዳል
ይሉት የለ ወይ ቀድሞም እርሱ ከአመጸኞች ጋር ይወዳጃል
መሪ አጥተው ለተበተኑ እውነተኛ እረኛ ነው
ይሰበስባል በፍቅር እጁ አቅፎ ያሞቃል በእቅፉ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists