Kishore Kumar Hits

Selam Desta - Ehedalew lyrics

Artist: Selam Desta

album: Alderaderem


እኔማ አለኝ ክብር (፪×)
እኔማ አለኝ አክሊል (፪×)
እኔማ አለኝ ክብር (፪×)
እኔማ አለኝ አክሊል (፪×)
ለጽዮን ስብሰባ ተጠርቻለሁ
ስራው በእኔ ተቆጥሮ ትገቢያለሽ ተብያለሁ
ኩነኔ የለብኝም ከሳሼስ ማነው
እርሱ በደሙ አጽድቆ ልጁ ተብያለሁ
ለጽዮን ስብሰባ ተጠርቻለሁ
ስራው በእኔ ተቆጥሮ ትገቢያለሽ ተብያለሁ
ኩነኔ የለብኝም ከሳሼስ ማነው
እርሱ በደሙ አጽድቆ ልጁ ተብያለሁ

ከግብጽ ምድር ቢወጡ
ወደ ተስፋይቱ ምድር
ወደ ውቧ ከነዓን ቢጠሩ
ብዙዎቹ ቀሩ ምድረ-በዳ
ሳይደርሱ ሳይገቡ ከእርስታቸው
ከግብጽ ምድር ቢወጡ
ወደ ተስፋይቱ ምድር
ወደ ውቧ ከነዓን ቢጠሩ
ብዙዎቹ ቀሩ ምድረ-በዳ
ሳይደርሱ ሳይገቡ ከግባቸው ጋር
ያ ተስፋ ከፊቴ ካለው ጋራ ፍጹም አይወዳደር
የኔማ አዲሲቱ ነው እየሩሳሌም
ያ ተስፋ ከፊቴ ካለው ጋራ ፍጹም አይነፃፀር
የኔማ አዲሲቱ ነው እየሩሳሌም

በበጉ ቅኔ በሙሴ ዜማ
እዘምራለሁ ከመላዕክት ጋራ
ክበር ክበር እያልኩ ፊቱ እቆማለሁ
እርሱ ስለረዳኝ እኔ እዘምራለሁ
በበጉ ቅኔ በሙሴ ዜማ
እዘምራለሁ ከመላዕክት ጋራ
ክበር ክበር እያልኩ ፊቱ እቆማለሁ
እርሱ ስለረዳኝ እኔ እዘምራለሁ
እሄዳለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ
እጠራለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ
እሄዳለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ
እጠራለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ
ከእነ አብርሀም ጋራ ከእነ ይስሀቅ
ከእነ እስራኤል ጋራ ከእነ ቅዱሳን
ከእነ አብርሀም ጋራ ከእነ ይስሀቅ
ከእነ እስራኤል ጋራ ከእነ ቅዱሳን
እሄዳለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ
እጠራለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ
እሄዳለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ
እጠራለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists