Kishore Kumar Hits

Kefa Midekesa - Andie Wodajie lyrics

Artist: Kefa Midekesa

album: Ande Wodajie Alegne, Vol. 3


አንድ ወዳጅ አለኝ
ለእኔ የሞተልኝ
ቅጣቴን የተቀጣህልኝ
አበሳዬን ከእኔ ወሰድክልኝ
ጌታ ተባረክልኝ
ኢየሱስ ተባረክልኝ
ጌታ ተባረክልኝ
ሙግቴን ተሟግቶ አሸንፎልኛል
ጠላቴ እንዳይከሰኝ ነጻ ነህ ብሎኛል
ይህን ወዳጄን ወዳጄ ነህ ያልኩት
ከማንም አብልጬ በልቤ የሾምኩት
አዝ፦ ለእኔ መልካም በማድረግ የታወቀው
መልካም በማድረግ የታወቀው
ለእኔ መልካም በማሰብ የታወቀው
መልካም በማሰብ የታወቀው
እርሱ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው
እርሱ ጌታዬ ነው ጌታዬ ነው
በምክሩ ግሩም ነው ነፍስን ይመልሳል
ከወዳጅ አብልጦ ወደ ልብ ይጠጋል
ደብቆ የያዘኝ እንዳልሆን የሌላ
የቅርቤ የምለው ማነው ከእርሱ ሌላ
አዝ፦ ለእኔ መልካም በማድረግ የታወቀው
መልካም በማድረግ የታወቀው
ለእኔ መልካም በማሰብ የታወቀው
መልካም በማሰብ የታወቀው
እርሱ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው
እርሱ ጌታዬ ነው ጌታዬ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists