Teshome Mitiku - Susegnash lyrics
Artist:
Teshome Mitiku
album: Zemen ( Ethiopian Contemporary Music
ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ
ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ
ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ
ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ
አመል ያለብኝ እኔ ሱሰኛሽ
አይቼሽ አልጠግብ ውጬ አልጨርስሽ
መውደድሽ ግሎ ልቤን ተኮሰው
እኔስ የት ልግባ ወዴት ልድረሰው
መውደድሽ ግሎ ልቤን ተኮሰው
እኔስ የት ልግባ ወዴት ልድረሰው
የፍቅርሽ ብዛት ልቤ ውስጥ ገብቶ
አርበተበተኝ አንጀቴን በልቶ
እኔ ሱሰኛሽ ላሞጋግስሽ
እንደ ዳዊቴም እስኪ ልድገምሽ
የፍቅርሽ ብዛት ልቤ ውስጥ ገብቶ
አርበተበተኝ አንጀቴን በልቶ
እኔ ሱሰኛሽ ላሞጋግስሽ
እንደ ዳዊቴም እስኪ ልድገምሽ
ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ እና ሐሙስ
አርብ ዓመት ሆነ ቀናቱ እስኪደርስ
ሱስ ያለኝ እኔን መች ያስችለኛል
ሲመሽ ሲነጋ አንቺን ይለኛል
ሱስ ያለኝ እኔን መች ያስችለኛል
ሲመሽ ሲነጋ አንቺን ይለኛል
እንዳንፀባራቂ ፊትሽ ሲያበራ
መቃው አንገትሽ ከሩቅ ሲጣራ
ተልፈሰፈስኩኝ ጉልበት አነሰኝ
ልቤ ተነካ መቻል አቃተኝ
እንዳንፀባራቂ ፊትሽ ሲያበራ
መቃው አንገትሽ ከሩቅ ሲጣራ
ተልፈሰፈስኩኝ ጉልበት አነሰኝ
ልቤ ተነካ መቻል አቃተኝ
አላስቀድስም ታቦት አላነግሥ
የኔ ውዳሴ አንቺ የኔ መቅደስ
ሱባዔ አልገባ መቆሚያም የለኝ
ምርኩዜም አንቺ እስኪ አንቺው ባርኪኝ
ሱባዔ አልገባ መቆሚያም የለኝ
ምርኩዜም አንቺ እስኪ አንቺው ባርኪኝ
ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ
ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ
ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ
ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ
ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ
ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ
ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ
ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ
ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist