በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ
አሃዱ አምላክ ብዬ ሰላምታ ላደርስ
ለፈጠርከኝ አንተ የላይኛው ንጉስ
እንዴት አለህ መጥቼ እስካይህ ድረስ
ያስደንቃል ያኗኗራቸው የጥንቱን
የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ የሶስቱ
ሶስት ናቸው በአካል በገፅ በስም
አንድ ናቸው በትዕዛዝ በግብር ፍፁም
ስላሴዎችም ይሄን ቅድመ አለም ሲኖሩን
አለም መፍጠር እሁድ በሰርክ ጀመሩን
ያን ጊዜውን ሰባት ፈጠሩ ቅፅበት
አስቀድሞ ሰማይና ምድርን በፊት
አራተኛ መላእክት እና ፅልመት
ሰባተኛ ማይና ንፋስ እሳት
በአርምሞ ይሄንን ሁሉ ፈጥረው
ተናገሩ ለይኩን ብርሀን ብለው
ሰኞ ጠዋት ውሀን ከፈሉት ከሶስት
አንደኛውን አዘቅት አረጉት ከምድር
ሁለቱን ሰማይ አረጉት ጠፍር
ማክሰኞን አብቅይ አሏት ምድርን
አበቀለች ሳር ቅጠሉን እህሉን
ረብዑም ረቂቅ ስራ ሲሰሩን
ከዋክብትን ፀሀይ ጨረቃ ፈጠሩ
ሀሙስም አልተውምና መፍጠር
የሚበሩ ክንፍ ያላቸውን ነገር
የማይበሩ የሚሄዱትን በእግር
በባህርም አሳ ጉማሬ ሳይቀር
አርብ ጠዋት አዳምን የኛን አባት
ምግበር ብለው በእነሱ አምሳል ሰሩት
በሰልስት ሄዋንን ፈጥረው ሰጡት
ትርዳህ ብለው ብቻውን ሆኖ ቢያዩት
የስላሴዎች የፍጥረታቸው ፍፃሜን
በሰባት ቀን ዳርቻ ሆነች ቅዳሜን
ስብሀት ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ለአለም እስከ ዘለዓለም አለም
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist