Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Fasiledes lyrics

Artist: Aster Aweke

album: Ćhewa


ሽር ሽር ሽር ሽር
ሽር ሽር ሽር ሸር በጎንደር
ሽር እንበል በጨፌው በወንዙ ዳር በአበባው

እንዋብ ባርባያ በራስ ዳሸን በር

ሁሉንም እንየው ና የኔ ቀብራራ

ነፍሴ ከነፍስ ጋር የሙጥኝ ተጣብቃ
ስትሄድ ተጨንቃ ስትመጣ ፈንድቃ
ቀኑን ስትሰራ ጎንደር ላይ ተሰማ
ልቤን የማለለው ተገኝቶ መተማ
መተማ መተማ መተማ መተማ
ሽር ሽር ሽር ሽር
ሽር ሽር ሽር ሸር

የእናቴ ሀገሬ
የእናቴ ሀገሬ ግርማ አንተ

የአባቴ ደማርቄ
ወንዛቸን አንድ ነው
ናልኝ ነጭ ወርቄ
ቅዳሜ ገበያ ገነት አደባባይ
ስናዳ ራስዳሸን እንሂድ ትክል ድንጋይ
መውደድ ሰውነቴ የዘዘዋል የዘንድሮ ገላ

ነፍሴ ከነፍስ ጋር የሙጥኝ ተጣብቃ
ስትሄድ ተጨንቃ ስትመጣ ፈንድቃ
ቀኑን ስትሰራ ጎንደር ላይ ተሰማ
ልቤን የማለለው ተገኝቶ መተማ
መተማ መተማ መተማ መተማ
ሽር ሽር ሽር ሽር
ሽር ሽር ሽር ሸር

የሐሚሲቷ
የያሙሲት ዳመና በጃን ተከል ፀሐይ

ጎንደር አደባባይ ብቅ አትልም ወይ

ከወንዝ ዳር ቆሜ ስመለከተው
አይኔን አጠገበው ጎንደር አበባው
በል አወንግዲህ እግሬ ባሻህ ተራመድ
ፍቅር ነው ጉዝጓዙ የጎንደር መንገድ

በል እንግዲህ ጥራ እንዳሻህ ተናገር
ፍቅር ነው ጉዝጓዙ የጎንደር መንገድ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists