Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Wuha Wuha lyrics

Artist: Aster Aweke

album: Ewedihalehu


ኧረ ውሀ ውሀ ውሀ አለሜ
ኧረ ውሀን የውሀ ጥም
ኧረ ውሀን
ኧረ ውሀ ውሀን አሰኘኝ
ብጠጣው ብራጨው እሚጠማኝ
ስትናፍቀኝ
አመመኝ አመመኝ ምነው ልቤን ደርሶ
ልትናፍቀኝ ነወይ ደሞ ባንተ ብሶ
አመመኝ አመመኝ አመመኝ አመመኝ
ቅዱስ ላሊበላ ያድነኝ ጨርሶ
መውደዱ አይሎ ናፍቆቱም እሳት ጎርሶ
አመመኝ አመመኝ አመመኝ አመመኝ

ውሀ ውሀ አሰኘኝ አንገበገበኝ
ፍቅሩ እንደ ውሀ ጥም እማይቆርጥልኝ
እሳት መዳኒቱ ውሀ ነው ዉህ ነው
የፍቅሩን ወላፈን አባይም አይዳኘው አይዳኘው
አመመኝ አመመኝ
የውሀ ጥም ሆንክብኝ
እህ እህ እህ እህ እህ እህ
ውሀ ውሀ የፍቅር ውሀ
የመውደድ ውሀ ውሀ ውሀ
እህ እህ እህ እህ እህ እህ አዬዬዬ

አመመኝ አመመኝ ምነው ልቤን ደርሶ
ልትናፍቀኝ ነወይ ደሞ ባንተ ብሶ
አመመኝ አመመኝ አመመኝ አመመኝ
ቅዱስ ላሊበላ ያድነኝ ጨርሶ
መውደዱ አይሎ ናፍቆቱም እሳት ጎርሶ
አመመኝ አመመኝ አመመኝ አመመኝ

የናፍቆት አለቃ የመውደድ እረኛ
ፈርዶ የሚያሰክነው የለውም ወይ ዳኛ
ጎተት ጎተት ይላል ፍቅር የያዘው
ሁለት ወር ኩዳዴን እንደምን ፆመው ፆመው
አመመኝ አመመኝ የውሀ ጥም ሆንክብኝ
እህ እህ እህ እህ እህ እህ
ውሀ ውሀ የፍቅር ውሀ
የመውደድ ውሀ ውሀ ውሀ
እህ እህ እህ እህ እህ እህ አዬዬዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists