Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Yamral lyrics

Artist: Aster Aweke

album: Fikir


ያገሬ ልጅ ሰውነቴ
ችላ አትበለኝ መድሀኒቴ
አትራቀኝ እንደ እንግዳ
አ አ እንደ ባዳ
የምወድህ ሰውነቴ
እንደምን ነህ አካላቴ
መንገድ ቢያለያየን
ናፍቆት ደጉ አገናኘን
ከፊት አዳራሽ ከማጀት
አልተመቸኝም መኝታ ቤት
አልተመቸኝም መኝታ ቤት
ከውጭ አድራለሁ ከዛፉ ስር
50 ሚሊዮን ኮከብ ስቆጥር
50 ሚሊዮን ኮከብ ስቆጥር
እሽሩሩ ብዬ መውደድ አዝያለው
ፍቅር ያልቅስ እንጂ መች አወርደዋለሁ
ፍቅር ያልቅስ እንጂ መች አወርደዋለሁ
ፍቅር ያልቅስ እንጂ መች አወርደዋለሁ
እሽሩሩ ብዬ አንዴ አዝዬዋለሁ
እሽሩሩ ብዬ ፍቅር አዝያለሁ
መች አወርደዋለሁ
የኔ መውደድ የኔ አለኝታ
አለህ ወይ የኔ ትዝታ
ወይ በለኝ የኔ ጌታ አ የኔ ጌታ
የኔ ፍቅር ሰውነቴ
ሚስጥሬ ነህ ውስጥ አንጀቴ
ምኔም ምኔም አካላቴ
የኔ ጠንበለል የኔ አይናማ
ቆንጆ አይታለፍ ባገሩማ
ቆንጆ አይታለፍ ባገሩማ
ናፍቆትህ ሆ እያለ ያንተውማ
ናፍቆትህ ሆ እያለ ያንተውማ
ትታየኛለህ በጭለማ
እሽሩሩ ብዬ መውደድ አዝያለው
ፍቅር ያልቅስ እንጂ መች አወርደዋለሁ
ፍቅር ያልቅስ እንጂ መች አወርደዋለሁ
ፍቅር ያልቅስ እንጂ መች አወርደዋለሁ
እሽሩሩ ብዬ አንዴ አዝዬዋለሁ
እሽሩሩ ብዬ ፍቅር አዝያለሁ
መች አወርደዋለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists