Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Munaye Munaye lyrics

Artist: Aster Aweke

album: Aster's Ballads


ሙናዬ ሙናዬ ሙናዬ ሙናዬ
ሙናዬ ሙናዬ አንተው ነህ ገላዬ
ፍቅርህ አሸነፈኝ መውደድህ የረታኝ
አይዞሽ በለኝ እንጂ ተው አታንገላታኝ
እያልኩኝ ስጨነቅ እኔ ምን ልሁን
ተው አንተዬ ፍቅርህ ያዝ ለቀቅ አይሁን

በመውደድ ስር ነኝ አይተህ ሁኔታዬን
አግዘኝ ፍቅርህን አልችልም ብቻዬን
አንተው ነህ በሽታዬ የጎዳኝ ፍቅር ነው
አልቻልኩም ብቻዬን ብታግዘኝ ምነው
ሙናዬ ሙናዬ ሙናዬ ሙናዬ
ሙናዬ ሙናዬ አትርሳኝ ገላዬ

እየዋለ ሲያድር ፍቅርህ አየለብኝ
ጤና አሳጥቶኛል መውደድህ ጠንቶብኝ
ስወድህ ውደደኝ ጠበቅ አርገህ ያዘኝ
አልችልም ብቻዬን ፍቅርህን አግዘኝ
ሙናዬ ሙናዬ ሙናዬ ሙናዬ
ሙናዬ ሙናዬ አትርሳኝ ገላዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists