Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Yene Konjo lyrics

Artist: Aster Aweke

album: Aster's Ballads


አጉል አጉል ሆነ ሆ' የእኔ አንጎል አልሰከነ
እንዴት ላመቻቸው እእእ የዋህ ልቤን አሰለቸው
እንዴት ላመቻቸው እእእ የዋህ ልቤን አሰለቸው
የተባባልነውን የኔ ቆንጆ
አንዴ ያምታታውና የኔ ቆንጆ
ዐይኔን ከልቤጋር የኔቆንጆ
አሟገተውና የኔቆንጆ
ምኞት ፍላጎቴን የኔቆንጆ
አዘበራረቀው የኔቆንጆ
ቸግሮኛል ሰዎች የኔቆንጆ
ኧረ እንዴት ልዝለቀው የኔቆንጆ
ምነው የኔቆንጆ
ምነው የኔቆንጆ
እግዚኦ ሊል የኔ ቆንጆ አቤት
እኔ ስመጥነው እሱ ልክ እያጣ
እኔ ሲብስብኝ ደሞ ሲቀናጣ
እንዳጀማመሩ አቃተው መጨረስ
ያሳመረ መስሎት ነገር ሊያደፈርስ
አያያዙን አያውቅ ነገር አገባቡን
ለራሱ ሲያደላ አስገመተው ልቡን
አጉል አጉል ሆነ የኔ አንጎል አልሰከነ
እንዴት ላመቻቸው እእእ የዋህ ልቤን አሰለቸው
እንዴት ላመቻቸው እእእ የዋህ ልቤን አሰለቸው
ያንተው ነኝ ያልኩኝ ለት የኔቆንጆ
ሊኮራ ከጀለ የኔቆንጆ
ልተወው ስቃጣው የኔቆንጆ
ጨርቁን እያስጣለው የኔቆንጆ
አመሉ አይጨበጥ የኔቆንጆ
የእሳትውሃ ሆኖ የኔቆንጆ
ያብከነክነኛል የኔቆንጆ
እሱም ተብከንክኖ የኔቆንጆ
ምነው የኔቆንጆ
ምነው የኔቆንጆ
እግዚኦ ሊል የኔ ቆንጆ አቤት
እኔ ስመጥነው እሱ ልክ እያጣ
እኔ ሲብስብኝ ደሞ ሲቀናጣ
እንዳጀማመሩ አቃተው መጨረስ
ያሳመረ መስሎት ነገር ሊያደፈርስ
አያያዙን አያውቅ ነገር አገባቡን
ለራሱ ሲያደላ አስገመተው ልቡን
አስገመተው ልቡን አስገመተው ልቡን
አስገመተው ልቡን አስገመተው ልቡን
አስገመተው ልቡን አስገመተው ልቡን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists