Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Ezoralehu lyrics

Artist: Aster Aweke

album: Sugar


አይኔ ካዬ ሁሉ
ቀልቤ ከገጀለ
የልቤን ማረፊያ
ዛሬም አላገኘሁ
አለሁ እንደተመኘሁ
ዛሬም እዞራላው
አለሁ እንደተመኘሁ
ዛሬም እዞራላው
ዛሬም እዞራላው
ዘመናዊ ሆኖ
የዘመኑ ፍቅር
ከፋራ ጋር በልቶ
ካራዳ ጋር ሲያድር
ባለፍኩበት ሃገር
በረገጥኩት ምንደር
ልቤ ማረፊያ አጣ
ሰው ፍለጋ ሲዞር
ሰው ፍለጋ ሲዞር

ከቤቴ በላይ
ከግራሮቹ
መውደድ ተኝቶ
ከነ ልጆቹ
ተነሳ ብዬ
ብቀሰቅሰው
ከነኔው ጭምር
ልቤን ጠቀሰው (እንዴት)
ወይ ልቤ ልቤ
ኩላሊቴን
እናቴን ጥሩ
መድሃኒቴን
እሷን ብታጡ
መቀነቷን
ፍቅር ደቆሰው
ጎን ጎኔን

ረብ ረብ ይላል ልቤ ብቻውን
ባህር ሰንጥቆ
ቆላ ደጋውን
ወይ ልቤ ልቤ
ልቤ ልብ የለው
ያን ሁሉ በደል
እንዴት ረሳው?
ረተተት ሸርተት ሸርተት እያለ
ኧረ ከዳኝ ከዳኝ
ልቤ ኮበለለ
አይኔ ካረፈበት
ቁመናው ካማረ
ልቤ ሸፈተ
ጥሎኝ በረረ።
እእህህ

እንደ ረጋ ወተት
ታግሶ እንዳደረው
ቀን ልጠብቅለት
እስካገኝ ብቁ ሰው።
እያየሁ ልለፈው
እስኪ ልታገሰው!
ለኔ ካለው አይቀር
እስኪ ልጠብቀው!
እስኪ ልጠብቀው!
ልጋብዝህ ልጋብዝሽ
በሚል ተጀምሮ
ፍቅር ከንፈር አልፎ
ከገባ ጉሮሮ!
ሆድ ቢሞላ ዛሬ
ላይገኝ ነገ አድሮ
ምን ፍቅር ይገኛል
ከግብዣ ቀጠሮ
ከግብዣ ቀጠሮ

ከቤቴ በላይ
ከግራሮቹ
መውደድ ተኝቶ
ከነ ልጆቹ
ተነሳ ብዬ
ብቀሰቅሰው
ከነኔው ጭምር
ልቤን ጠቀሰው (እንዴት)
ወይ ልቤን ልቤን
ኩላሊቴን
እናቴን ጥሩ
መድሃኒቴን
እሷን ብታጡ
መቀነቷን
ፍቅር ደቆሰው
ጎን ጎኔን

ረብ ረብ ይላል ልቤ ብቻውን
ባህር ሰንጥቆ
ቆላ ደጋውን
ወይ ልቤ ልቤ
ልቤ ልብ የለው
ያን ሁሉ በደል
እንዴት ረሳው?
ረተተት ሸርተት ሸርተት እያለ
ኧረ ከዳኝ ከዳኝ
ልቤ ኮበለለ
አይኔ ካረፈበት
ቁመናው ካማረ
ልቤ ሸፈተ
ጥሎኝ በረረ።
እእህህ
ከቤቴ በላይ
ከግራሮቹ
መውደድ ተኝቶ
ከነ ልጆቹ
ተነሳ ብዬ
ብቀሰቅሰው
ከነኔው ጭምር
ልቤን ጠቀሰው (ወይኔ)
ወይ ልቤ ልቤ
ኩላሊቴን
እናቴን ጥሩ
መድሃኒቴን
እሷን ብታጡ
መቀነቷን
ፍቅር ደቆሰው
ጎን ጎኔን
ጎን ጎኔን
ኧረ ልቤን ጠቀሰው
ጎን ጎኔን
ኧረ ልቤን ጠቀሰው
ውይ ውይ
ጎን ጎኔን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists