Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Sew Mehonne lyrics

Artist: Aster Aweke

album: Sugar


እስቲ ልነሳና ልያዘው መንገዴን

መውደድን ፍለጋ ስደተኛውን

ለመንገደኛ ሰው አይነፍጉም ስንቁን

ናፍቆት እንዳይበላው አንጀት አንጀቱን

የማይጠፋ የሚጠፋብኝ

የማይከፋው የሚከፋብኝ

የማይቸግር የሚቸግረኝ

የሚሆነው የማይሆንልኝ
አሀሀሀሀ አወይ ሰው መሆኔ

የማይመች የሚመቸኝ

ያልበላሁት የሚያጠግበኝ

ያለበስኩት የሚሞቀኝ

በዕለተ ጀምበር የሚያስደስተኝ
አሀሀሀሀ መውደድ ሲይዘኝ

የፍቅር ቁስሉ የማይሽርልኝ

ዞሮ መቃጠሉን የማይሆንልኝ

ስቀርብም ስወድም እየጠረጠርኩኝ
አሀ አሄሄ አሀ አሀሀ
ኦሆይ አሄሄይ እምህ አሀሀ
አማርረውና አምላኬን በፀና

ተመስገን እላለሁ መልሼ እንደገና

ብዙ የሰው ፍጡር እንደዚህ ነውና
አሀ አሄሄ አሀ አሀሀ
እምህ አሄሄይ እምህ አሀሀ

ሰው ጊዜ አይቶ የሚጥለኝ

የታመነው የሚከዳኝ
የሆንኩለት የማይሆነኝ
ሁልጊዜ የሚመሽብኝ
አሀሀሀሀ አወይ ሰው መሆኔ

አማርረውና አምላኬን በፀና
ተመስገን እላለሁ መልሼ እንደገና
አማርረውና አምላኬን በፀና

ተመስገን እላለሁ መልሼ እንደገና
እንደገና እንደገና እንደገና እንደገና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists