Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Yale Sime lyrics

Artist: Aster Aweke

album: Ebo


እንዳው ያለ ስሜ ስም ሲሰጠኝ ኖሮ
በየደረስበት ሲጣጣለኝ ዞሮ
እንዲነች እንዲያ ነች ሲለኝ መክረሙ ኣንሶ
ኣይን ኣዉጥቶ መጣ ደሞ ተመልሶ
ተ መ ል ሶ ተመልሶ
ያወራ ጀመረ ኣንጃና ግራንጃ
የዘንድሮው ደሞ የታየዉን እንጃ
እንጃ እ ን ጃ እ ን ጃ ኸ እንጃ አሃ
ኣስከፋቺኝ ኣለ አሳዝኖኝ ሄዶ
የወራት ድካሜን ባንድ ጀንበር ንዶ
ንዶ ን ዶ ን ዶ ኸ ንዶ ኦሆ
እራሱ በድሎ እራሱ እለቀሰ
ባሉባልታ ፈረስ አገር ኣደረሰ
እራሱ በድሎ እራሱ እለቀሰ
ባሉባልታ ፈረስ አገር ኣደረሰ
እ እእ
ባሉባልታ ፈረስ አገር ኣደረሰ
ስሙኝ ስሙኝ ኣለ ቆሞ ኣደግድጎ
እኔን በደለኛ እሱን ጭምት ኣርጎ
መቼም አይዘጋ ጆሮበር የለዉ
እስቲ ይሰማለት ዛሬም የሚለው
ኸ የሚለው የሚለው
መክዳቱ እንይበቃኝ ድንገት መገለጡ
ጉድ ያሰኘኝ ጀመር የስም ኣሰጣጡ
ጉዴ ጉ ዴ ጉ ዴ ህይ ጉ ዴ
ካንድ ያልጠና ነገር ካልሆነልክ እማ
ይፋ ላዉጣህና በደልህ ይሰማ
ይሰማ ይ ሰ ማ ይሰማኸይ ይሰማአሃ
እራሱ በድሎ እራሱ እለቀሰ
ባሉባልታ ፈረስ አገር ኣደረሰ
እራሱ በድሎ እራሱ እለቀሰ
ባሉባልታ ፈረስ አገር ኣደረሰ
እ እእ
ባሉባልታ ፈረስ አገር ኣደረሰ
እንዳው ያለ ስሜ ስም ሲሰጠኝ ኖሮ
በየደረስበት ሲጣጥለኝ ዞሮ
እንዲነች እንዲያ ነች ሲለኝ መክረሙ ኣንሶ
ኣይን ኣዉጥቶ መጣ ደሞ ተመልሶ
ተ መ ል ሶ ተመልሶ
እንዲነች እንዲያ ነች ሲለኝ መክረሙ ኣንሶ
ኣይን ኣዉጥቶ መጣ ደሞ ተመልሶ
ተ መ ል ሶ ተመልሶ
ተ መ ል ሶ ተመልሶ
አይን ኣውጥቶ መጣ ደሞ ተመልሶኸኸ
ተ መ ል ሶ ተመልሶ
ተመልሶ ተመልሶ ተመልሶ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists