Kishore Kumar Hits

Neway Debebe - Teteyeki Was lyrics

Artist: Neway Debebe

album: Best of Neway Debebe Collection


አረግ አረግ አረግ አረግን ምን ይደረግ
ብቻ ምን ይደረግ
አይኗ ሰዉ ገደለ
ጥርሷ እያባበለ
ሽንጧን ያየ ወዶ
በዚያዉ ቀረ ወርዶ
በደሏ ቢከፋ ዋሷ ሚሆን ጠፋ
በደሏ ቢከፋ የሚዋሳት ጠፋ

አሆየዉ ጉብል እሷን እሷን እያልኩ አሆየዉ ጉብል ማዶ ማዶ ሳይ
አሆየዉ ጉብል ቀኑም መሻሸና አሆየዉ ጉብል ጠቆረ ሰማይ
አሆየዉ ጉብል ድካሜን ላታዉቀዉ አሆየዉ ጉብል ላትለኝ ጉዳይ
አሆየዉ ጉብል ተንከራተትኩላት አሆየዉ ጉብል በዛብኝ ስቃይ
ተጠያቂ (ዋስ) መልስሽ ይዣለዉ (ዋስ)
አልረታም (ዋስ) እረታለዉ (ዋስ)
ሸንጎ ለፍርድ (ዋስ) እወጣለዉ (ዋስ)
አለቃትም (ዋስ) ጠይቃለዉ (ዋስ)
ዋስ ዋስ ዋስ ዋስ ዋስ
ዬ ዬ ዬ ዬ ዬ

ጉድ ነዉ የሷስ ዉበት ስንቱን አጋደለ
በየደረሰበት እጥፍ ዘርጋ እያለ
እያስተካከለ ሲፈጥራት መዋሉ
ዉበት ሲያርከፈክፍ ሲያድላት ነዉ አሉ
የአስታራቂ የገላጋይ
የሚያስማማ ባለጉዳይ
እጄን ሰጠዉ ፍቅሯን ታሳይ
ሰርግ አይባል ወይ ጠለፋ
ተከትሏት ልቤም ጠፋ
ቅር ሳይሰኝ ሳይከፋ
ቅር ሳይሰኝ አይከፋ
ቅር ሳይሰኝ አይከፋ

አረግ አረግ አረግ አረግን ምን ይደረግ
ብቻ ምን ይደረግ
አይኗ ሰዉ ገደለ
ጥርሷ እያባበለ
ሽንጧን ያየ ወዶ
በዚያዉ ቀረ ወርዶ
በደሏ ቢከፋ የሚዋሳት ጠፋ
በደሏ ቢከፋ የሚዋሳት ጠፋ

አሆየዉ ጉብል እቺን ማን ይሏታል አሆየዉ ጉብል አይደለች የዋዛ
አሆየዉ ጉብል አይታ ከምታልፈዉ አሆየዉ ጉብል የምትጥለዉ በዛ
አሆየዉ ጉብል ያ ጦረኛ ሽጧ አሆየዉ ጉብል የሚነሰነሰዉ
አሆየዉ ጉብል ሰዉ ገሎ ተይዟል አሆየዉ ጉብል ማነዉ የሚዋሰዉ
ተጠያቂ (ዋስ) መልስሽ ይዣለዉ (ዋስ)
አልረታም (ዋስ) እረታለዉ (ዋስ)
ሸንጎ ለፍርድ (ዋስ) እወጣለዉ (ዋስ)
አለቅሽም (ዋስ) ጠይቃለዉ (ዋስ)
ዋስ ዋስ ዋስ ዋስ ዋስ

ሆንኩኝ ህመምተኛ አላመለጥኩ ከእዳ
እቺ ሰበበኛ ከሰዉ ራስ መች ወርዳ
እስቲ ጠይቁልኝ ከሰማች ምን አልባት
የታመመ ሚያድን ቅመመም በእጇ እንዳላት
የአስታራቂ የገላጋይ
የሚያስማማ ባለጉዳይ
እጄን ሰጠዉ ፍቅሯን ታሳይ
ሰርግ አይባል ወይ ጠለፋ
ተከትሏት ልቤም ጠፋ
ቅር ሳይሰኝ ሳይከፋ
ቅር ሳይሰኝ አይከፋ
ቅር ሳይሰኝ አይከፋ
ቅር ሳይሰኝ አይከፋ

አይይይይይ እንዲያ እንዲያ
እንዲያ እንዲያ እንዲያ እንዲያ
አየኋት አዎ አየኋት
አይኔ አይቶ መቼ አለፋት
በልቤ ተዝናኝበት
እንዲያ እንዲያ እንዲያ እንዲያ እንዲያ
አረ እንዲያ እንዲያ እንዲያ እንዲያ እንዲያ
እንዲያ እንዲያ እንዲያ እንዲያ እንዲያ
እንዲያ እንዲያ እንዲያ እንዲያ እንዲያ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists