Kishore Kumar Hits

Michael Belayneh - Timechi Endehu lyrics

Artist: Michael Belayneh

album: Nafkot Ena Fikir


ትመጪ እንደዉ እያልኩ ሌት ተቀን ናፋቂ
ሰርክ የማይታክተኝ አለዉሽ ጠባቂ
ፍቅር ተደግፌ ቃልኪዳን ታቅፌ
ትመጪ እንደዉ እያልኩ ክፍት ነው ደጃፌ
አትቀርም እላለዉ በመላ በጥበብ
ምን ቀን እየገፋ እድሜዬን ብታለል
ቆፈን ቢገርፈኝም ጥብቃዬ በዝቶ
እኔ ግን እዛዉ ነኝ አላጎደልኩ ከቶ
ትመጪ እንደዉ ትመጪ እንደዉ
አለው እኔ ሳላጎል በፍቅር እንዳለዉ
ትመጪ እንደዉ ትመጪ እንደዉ
አለው እኔ በፍቅር አለሁኝ እንዳለዉ
በናፍቆትሽ እሣት ነድጄ ሳልከስል
ባይንሽ በጠረንሽ መልሼ እንዳገግም
ሣዜም እኖራላዉ ሥኖር ስደጋግም
ካለዉበት ድረስ እግርሽ ዕንዲረዝም
ልምጣ ያልሽ እንደሆን ቀና ነዉ ጎዳና
ልቤ ተመላልሶ ደልድሎታልና
ምኞት የማይደክመዉ ልቤ ልበ ብርቱ
ትዝታም አይደለ ተስፋ ነዉ ቅኝቱ
ትመጪ እንደዉ ትመጪ እንደዉ
አለዉ እኔ ሳላጎል በፍቅር እንዳለዉ
ትመጪ እንደዉ ትመጪ እንደዉ
አለዉ እኔ በፍቅር አለሁኝ እንዳለዉ
ትመጪ እንደዉ ትመጪ እንደዉ
አለሁ እኔ ሳላጎል በፍቅር እንዳለዉ
ትመጪ እንደዉ ትመጪ እንደዉ
አለሁ እኔ በፍቅር አለሁኝ እንዳለዉ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists