Michael Belayneh - Tinita lyrics
Artist:
Michael Belayneh
album: Nafkot Ena Fikir
መጠን አልፎ ፍቅሬ ከአቅምሽ ተርፎ
ቸል ይለኝ ጀመረ ልብሽ ሞልቶ
የፍቅር ግለት እያሞቀው
መውደዴ ልብሽን ጨነቀው
ፍቅር ሞልቶ ሲፈስ አየው
እኔን እኔን እኔን እኔን እልሻለው
(እኔን እኔን እኔን)
እኔን እኔን እኔን እኔን እልሻለው
(እኔን እኔን እኔን)
በፍቅር ትንታ ተቸግረሽ አየው
በፍቅር ትንታ ተቸግረሽ አየው
መሰረቱ የፍቅር ነው መስጠቱ
ለመቀበል አይደለም መጎምዠቱ
ሳይሰለቸኝ ሰጠው የፍቅር ስጦታ
እኔን እያልኩ ቢበዛም ትንታ
አድምጪው ልብሽን ላንዳፍታ
እኔን እኔን እኔን እኔን እልሻለው
(እኔን እኔን እኔን)
እኔን እኔን እኔን እኔን እልሻለው
(እኔን እኔን እኔን)
በፍቅር ትንታ ተቸግረሽ አየው
በፍቅር ትንታ ተቸግረሽ አየው
ፍቅር ቡራኬ እንጂ ከላይ የታደለ
ሲያምረን የምንገዛው አይደል የትም ያለ
አወቀሽ ፍቅሬ ገረም ስቶ
ከበበሽ ደመና ሊሸሽግሽ ሽቶ
እኔን እኔን እኔን እኔን እልሻለው
(እኔን እኔን እኔን)
እኔን እኔን እኔን እኔን እልሻለው
(እኔን እኔን እኔን)
በፍቅር ትንታ ተቸግረሽ አየው
በፍቅር ትንታ ተቸግረሽ አየው
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist