Kishore Kumar Hits

Tsegaye Eshetu - Sendekalama lyrics

Artist: Tsegaye Eshetu

album: Best of Tsegaye Eshetu


ህይወቱን ሸልሞ በደሙ ላስዋበሽ
በደሙ ላኖረሽ
ሰንደቅ አላማቸን ኑሪ እየመሰከርሽ
ኑሪ እየተናገርሽ
ሀገር እና ሰንደቅ ነፃነት ከሌለ
ቤት ሰርቶ ማረፊያ ወልዶ መክበድ የለ
ሰንደቅ ነች ሀይማኖት አላማ ነች እምነት
አርማ የለሽ ዜጋ የለዉም ነፃነት
አናሳፍርሽም ታሪክ ይወቅሰናል
ዜጎችሽ ዋርዲያ ዘብ ሆነን ቆመናል
ዘብ ሆነን ቆመናል
አእዋፍም ይበራሉ እንሰሳትም ይዝናናሉ
ብርቁም ድንቁም ይደምቃሉ
እንደ ቆመች ያበስራሉ በመኖሯም ይኖራሉ
እንደ ቆመች ያበስራሉ በመኖሯም ይኖራሉ
ለሶስት ሺ ዘመን የደም የአጥንት አሻራ ምልክት
የተስፋ የፀጋ የለም ሀገር የታሪክ መስታወት
ሰንደቃችን ኑሪ ኑሪ ኮርተሸ አኩሪ
ሰንደቃችን ኑሪ ኑሪ ኮርተሸ አኩሪ
ህይወቱን ሸልሞ በደሙ ላስዋበሽ
በደሙ ላኖረሽ
ሰንደቅ አላማቸን ኑሪ እየመሰከርሽ
ኑሪ እየተናገርሽ
አበዉ በደማቸዉ ያቆዩት ቅርሳችን
የክብር የነፃነት ምልክት ልብሳችን
ኩሪ በአረንጓዴዉ በብጫዉ በቀይ
ብናልፍም ይተካል የሚሞት በክብርሽ
ከቀስተ ዳመናዉ እኩል አብረቅርቀሽ
ዝንተ አለም ኑሪ እየተዉለበለብሽ እየተዉለበለብሽ
በአንቺ ጥላ ተከልዬ በአርማችን ተለይተን
ሰላም ተስፋን ተጐናፅፈን
ባንዲራችን አለንልሽ አደራችን ዉርሳችን ነሽ
ባንዲራችን አለንልሽ አደራችን ዉርሳችን ነሽ
ለሶስት ሺ ዘመን የደም የአጥንት አሻራ ምልክት
የተስፋ የፀጋ የለም ሀገር የታሪክ መስታወት
ሰንደቃችን ኑሪ ኑሪ ኮርተሸ አኩሪ
ሰንደቃችን ኑሪ ኑሪ ኮርተሸ አኩሪ
ሰንደቃችን ኑሪ ኑሪ ኮርተሸ አኩሪ
ሰንደቃችን ኑሪ ኑሪ ኮርተሸ አኩሪ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists