Kishore Kumar Hits

Tsegaye Eshetu - Tekelekele Alu lyrics

Artist: Tsegaye Eshetu

album: Best of Tsegaye Eshetu


ተከለከለ አሉ ተከለከለ አሉ
ተከለከለ አሉ ተከለከለ አሉ
በርሽ ያለ አመሉ
ምነዉ መዘጋቱ ምነዉ መከልከሉ
ምነዉ መዘጋቱ ምነዉ መከልከሉ
ለወደደሽ ሁሉ
ጉዳዬ ሳይሞላ ድንገት ሳላስብ
ከኔ ወዲያ ሌላ አሰርሽ ማተብ
እኔ ጭምት ስባል በስምሽ ስጣገር
ማንን ተካሽብኝ ወየዉ የሰዉ ነገር
ይዋል ይደር እንጂ ሆዴን እያመመዉ
ትዝብት ነዉ ትርፉ ከተካሁብሽ ሰዉ
ማን ይፈርድብኛል ብልሀት ባበጅላት
ነይ ስላት ከራቀች ህጅ ብዬ ብተዋት
እኔም አልበለጥ ተገምቼም አልቀር
እሞክረዋለዉ የአንቺን ከሰዉ ባገኝ
እድሌ ቢከፋ እንዲያዉ ባይሞላልኝ
ያለመድኳት እርግብ ሌላ መረጠብኝ
እየዉ ደማዬ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬን አይ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬን አይ እየዉ ደማዬ
እዩልኝ ዉበቷን አጥር ሲሸልማት
የአባት ባለ ጋራ የእናት ባላንጣ አላት
ታመጣለች ሲባል ሸጋ ለዝምድና
ታራርቅ ጀመረ ስስት ሆነችና
እራብ ያለ እንደሆን እህል ይጐረሳል
ገላም ሲበርደዉ ጋቢ ይደረባል
የድካም አቀበት በእንቅልፍ ይዘለቃል
የፍቅር አባዜ በምን ይመከታል
ወትሮም እኔ ነበርኩ መከለያ አጥሯ
እሷ አትንኩኝ ስትል ሁሉን እሽ ባይዋ
አይከለክሉትም የቆየን ወዳጅ
ባይሆን ወንድም አርገዉ ያፅናኑታል እንጂ
እየዉ ደማዬ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬን አይ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬን አይ እየዉ ደማዬ
ተከለከለ አሉ ተከለከለ አሉ
ተከለከለ አሉ ተከለከለ አሉ በርሽ ያለ አመሉ
ምነዉ መዘጋቱ ምነዉ መከልከሉ
ምነዉ መዘጋቱ ምነዉ መከልከሉ
ለወደደሽ ሁሉ
ማስታወሻ ነዉ ወይ ለእድሜዋ መጨመር
ዉበቷ ሲያጓጓ አጥር ናት ጥናግር
የልጅነት ወጓን እናቷ ያዩላት
ወደ ምንጭ አትወርድ ወይ ገበያ የላት
እራብ ያለ እንደሆን እህል ይጐረሳል
ገላም ሲበርደዉ ጋቢ ይደረባል
የድካም አቀበት በእንቅልፍ ይዘለቃል
የፍቅር አባዜ በምን ይመከታል
ከእንጊድህ ሰዉ ብሎ ማን ይሆን የሚያምናት
አላት ያሉት ጠፍቶ ሁሉም ሲዘረፋት
ማተብሽኝ አላልተሸ አድርገሽ ባትሄጂዉ
ሴቱስ ታመነበት ወንዱን አሳማሽዉ
እየዉ ደማዬ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬን አይ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬን አይ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬን አይ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬ እየዉ ደማዬ
እየዉ ደማዬን አይ እየዉ ደማዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists