Kishore Kumar Hits

Tsegaye Eshetu - Ehiedalehu Harer lyrics

Artist: Tsegaye Eshetu

album: Best of Tsegaye Eshetu


ድሬ ሀረር
ድሬ ሀረር
እሄዳለሁ ሐረር ባቡር ተሳፍሬ
ያችን ጉብል ወጣት አያታለዉ ድሬ
በሹሩባዋ ላይ ዛጎል ያሰረችዉ
ማሽላ ጠባቂ ሐረር ላይ ያለችዉ
ድሬ ላይ ያለችዉ
ዋኔ ዋኔ እያለች በእምባ ስትለየኝ
ከልቤ አልጠፋ አለች
ድሬ ድሬ አሰኘኝ ድሬ ድሬ አሰኘኝ
መገን የድሬ ልጅ ፀባይ ምግባራቸዉ
እንግዳ ያለምዳል አቀራረባቸዉ
ከማሽላዉ ዛላ ቀንጥሳ ጋብዛኝ
ተላወሰ ሆዴ መዉደድ ዘርታብኝ
አቦ ሰላም ያግባህ ብላ እንደሸኘችኝ
እንዳይጨንቀኝ ምነዉ በተከተለችኝ
አሃሃ ሀ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀሀ ሀሀ
እሄዳለሁ ሐረር ባቡር ተሳፍሬ
ያችን ጉብል ወጣት አያታለዉ ድሬ
በሹሩባዋ ላይ ዛጎል ያሰረችዉ
ማሽላ ጠባቂ ሐረር ላይ ያለችዉ
ድሬ ላይ ያለችዉ
ዋኔ ዋኔ እያለች በእንባ ስትለየኝ
ከልቤ አልጠፋ አለች
ድሬ ድሬ አሰኘኝ ድሬ ድሬ አሰኘኝ
ኮልተፍ ኮልተፍ ሲል ጣፋጭ አንደበቷ
ቃሏም ይናፍቃል እንኳን ደም ግባቷ
እፎይ ብዬ አልተኛ ሰላምታ ልኬብሽ
እንዳሻኝ አርጉልኝ አልል እንደሰዉ ሆኜ
ምን ለብሼ ልምጣ እስኪ አንቺዉ ላኪብኝ
ወጉን አላዉቅበት ሽርጥ አያምርብኝ
አሃሃ ሀ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀሀ ሀሀ
እሄዳለሁ ሐረር ባቡር ተሳፍሬ
ያችን ጉብል ወጣት አያታለዉ ድሬ
በሹሩባዋ ላይ ዛጎል ያሰረችዉ
ማሽላ ጠባቂ ሐረር ላይ ያለችዉ
ድሬ ላይ ያለችዉ
ዋኔ ዋኔ እያለች በእንባ ስትለየኝ
ከልቤ አልጠፋ አለች
ድሬ ድሬ አሰኘኝ ድሬ ድሬ አሰኘኝ
ከዞርኩበት ሁሉ ድሬን ምን አደላት
እንደፍራፍሬዉ የሰዉ ዉብ ሸጋ አላት
ከድሬ ልጅ ፍቅር ትዝታ የያዘዉ
አዋሽ ቁርስ አይበላ ሂርና ምሳ የለዉ
እዩት ብርቱ ልቤን መዉደድ ያከነፈዉ
ከባቡሩ ቀድሞ አዳሩ ድሬ ነዉ
አሃሃ ሀ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀሀ ሀሀ
አሃሃ ሀ አሃሃ ሀ አሃሃ ሀሀ ሀሀ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists