Kishore Kumar Hits

Tsegaye Eshetu - Lesergua Teterahu lyrics

Artist: Tsegaye Eshetu

album: Best of Tsegaye Eshetu


ሸጌ የሰርግሽ እለት ጥሪዉ ደርሶኛል አመስግኛለዉ
ምንም ባዝን ቢሰማኝ ምን አቅም አለኝ
ምን እፈጥራለዉ ሲዘፈን ሲደለቅ ቃል ከተሸከመች እሸኝሻለዉ
ዉቢት የሰርግሽ እለት ጥሪዉ ደርሶኛል አመስግኛለዉ
ምንም ባዝን ቢሰማኝ ምን አቅም አለኝ
ምን እፈጥራለዉ ሲዘፈን ሲደለቅ ቃል ከተሸከመች እሸኝሻለዉ ሲዘፈን ሲደለቅ ቃል ከተሸከመች እሸኝሻለዉ

አሀUU ጠልፌ አልወሰድኳት
መኩሪያ ጥይት የለኝ
እህህህ አስጥዬ አላስቀራት ትከሻዬ አነሰኝ ትከሻዬ አነሰኝ
አሀሀሀ አብሬያት አልሄድ አምናኝ ተማምኘት
እህህህ ለሰርጓ ተጠራሁ ለሌላ ሲድሯት ለሌላ ሲድሯት
የሷ ወግ የኔ ሀዘን አ ተገጣጠመና የኔ ሸጋ
ሰርገኛዉ አዘነና ሁለት ኖረና የኔ ቆንጆ
ባልእንጀራ አይግፋሻ ተብሎ ሲዘፈን ኔ ሸጋ
የኔን ማን አየልኛ የፍቅሬን ሰቀቀን የኔ ቆንጆ

ወይ ይዤሽ መክረሜ ላትሆኚኚ ላልሆንሽ
አልሰማም ዙሪያዬ አስጥዬ ካነስኩሽ
ከዚ በላይ ምን ሊያሳዝን የሰዉ ነገር
እድሜ የሰጠዉ ብዙ ይችላል ምን ቢቸገር
በትዝታ ስኮራመት ያለአዛኝ ጣለቺኝ
ትዳሯን ያሙቀዉ የምላትም የለኝ

ጉብል የሰርግሽ እለት ጥሪዉ ደርሶኛል አመስግኛለዉ
ዉቢት አዲሱ ቤትሽን የአለም ያርግልሽ መርቄሳለዉ
ነጥለዉሽ ከኔ ሰተዉሽ ለሌላ ምን አደርጋለዉ
ነጥለዉሽ ከኔ ሰተዉሽ ለሌላ ምን አደርጋለዉ

አሀሀሀ አማላጄን ታዘብኩ በአንቺ የተነሳ
እህህህ ሁሉም ቀለለብኝ ሚዛን አያነሳ ሚዛን አያነሳ
አሀሀሀ በይ ተይዉ በይ ተይዉ ይቅር ምን ያደርጋል
እህህህ እንኳን የወጠኑት የያዙት ይቀድቃል
የያዙት ይቀድቃል
አልገባም ከዳሱ ድግሱም ምኔ ነዉ የኑ ሸጋ
ትከሻዬም አይሞቅ አይጥመኝ እስክስታ የኔ ቆንጆ
ሆ ማለት እልልታ ላገኘሽ ብቻ ነዉ የኔ ሸጋ
ተነጥቆ ላጣማ መች እዬዬ አነሰዉ የኔ ቆንጆ

ለሁሉም አትሞላም አለም ጎዶሎ ነች
ደስታና ሀዘንን ታካፍለዋለች
ደሞ ካለያየን ሆዴ የእድል ነገር
ይቅናሽ እንጂ ምን ሊወጣኝ ምን ልናገር
ስትሸኝ ልዘን እንጂ ያለ ሰዉ ጥለሽኝ
በአንቺ የሚተካ ማካካሻም የለኝ

ሸጌ የሰርግሽ እለት እኔዉ ልቅር እንጂ ተጠርቻለዉ
አለም ነዉ ወግ ማእረግሽ ቤትሽ ሲዘፈን ሳለቅስ ዉያለዉ
አድባር ትቀበልሽ እኔ ባዳሽ ነኝ እርቄሻለዉ
አድባር ትቀበልሽ እኔ ባዳሽ ነኝ እርቄሻለዉ

አሀሀሀ በእምት በሃይማኖት በማተብ አንድ ሆነን
እህህህ የምን ዱብ እዳ ነዉ ሳንስብ የለየን ሳንስብ የለየን
አሀሀሀ የዘር ዝራዝሯን ከዘሬ ቂም የለውም
እህህህ ሳትወድ ከኔ ለይዋት ምርጫዋን ተጭነዉ
ምርጫዋን ተጭነዉ
ማ ተብዬ ልምጣን ሳስብ ልጠይቅሽ የኔ ሸጋ
አብሮ አደግ ወዳጄ ናት ብል ይከፋል ባልሽ የኔ ቆንጆ
በቃ ተራራቅና ያሰብነዉም ቀረ የኔ ሸጋ
ምኞት ዉጥናችን አይ መች ለዚ ነበረ የኔ ቆንጆ

አይጠፋም እንደእኔ እጣ የደረሰዉ
ጠብቆ ያቆየዉን ያሳለፈ ለሰዉ
ደሞ ሆዴን ያቃጥል እንጂ የአንቺ ነገር
ያጣ አያምር አድማጭ የለዉ ምን ቢናገር
ተኮራምቶ አይዘልቀዉም ያለ ሰዉ ብቻዉን
የሆዴ ሀዘን በዛ አጣ መፅናኛዉን

የሆዴ ሀዘን በዛ አጣ መፅናኛዉን
የሆዴ ሀዘን በዛ አጣ መፅናኛዉን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists