Kishore Kumar Hits

Tsegaye Eshetu - Alasgedidshem lyrics

Artist: Tsegaye Eshetu

album: Best of Tsegaye Eshetu


ጥንትም ላይሆንልሽ እንዲያው ተቸገርሽ
እኔስ አይገርመኝም ወዶ መጥላትሽ
ጥለሽኝ ብትሔጂ ካልከበደሽ ግፉ
አላስገድድሽም ትዝብት ነው ትርፉ
ጥንትም ላይሆንልሽ እንዲያው ተቸገርሽ
እኔስ አይገርመኝም ወዶ መጥላትሽ
ጥለሽኝ ብትሔጂ ካልከበደሽ ግፉ
አላስገድድሽም ትዝብት ነው ትርፉ
ፍቅርም ካልቀደመ ከገንዘብ ከሓብቱ
ቁምነገር የለውም መዋደድ በከንቱ
ካንቺማል ደብቀው ችዬ ማልሸሽግሽ
መውደዴን ነው እኔ መቼም የማልነጥቅሽ
በአይኔ ሳይሰሰት በእጄም ሳልነጥለው
የማላውቀው ልብሽ ምንግዜም ፍቅሬ ነው
ቢከብድም ባይከብድም በምድር ውለታዬ
ላንቺ የማቀርበው ይህ ነው ስጦታዬ
ቁምነገር ነው ብዬ ውለታን ውያለው
አላስቀየምኩሽም ቃሌን አክብሬያለው
በደል ከቁምነገር ከበዛብሽማ
አቻሽን ፈልጊ ላንቺ እንደሚስማማ
በደል ከቁምነገር ከበዛብሽማ
አቻሽን ፈልጊ ላንቺ እንደሚስማማ
ጥንትም ላይሆንልሽ እንዲያው ተቸገርሽ
እኔስ አይገርመኝም ወዶ መጥላትሽ
ጥለሽኝ ብትሔጂ ካልከበደሽ ግፉ
አላስገድድሽም ትዝብት ነው ትርፉ
ጥንትም ላይሆንልሽ እንዲያው ተቸገርሽ
እኔስ አይገርመኝም ወዶ መጥላትሽ
ጥለሽኝ ብትሔጂ ካልከበደሽ ግፉ
አላስገድድሽም ትዝብት ነው ትርፉ
አንዱ ብሩን ሲቸር ሌላው ከየት ያመጣል
የኔ ልብ ሐብታም ነው እምነቱን ይሰጣል
ዛሬም አለኝ ፍቅር የያዝኩት ሰስቼ
መቼም በዚህ በኩል አላውቅም ደህይቼ
ጎጆማ ጓዳማ ቤትማ ነበረኝ
ማዕድ የሚያቋርስ ሰው ነው የቸገረኝ
ዛሬ እኔን ዘንግቶ ገላሽ ሰው ቢለምድም
ትላንት ወደሽኛል ክፉሽን አልፈቅድም
ቁምነገር ነው ብዬ ውለታን ውያለው
አላስቀየምኩሽም ቃሌን አክብሬያለው
በደል ከቁምነገር ከበዛብሽማ
አቻሽን ፈልጊ ላንቺ እንደሚስማማ
በደል ከቁምነገር ከበዛብሽማ
አቻሽን ፈልጊ ላንቺ እንደሚስማማ
ጸጸቱ እስኪሰማሽ ጨክኔሽ ብትቆርጪ
ለኔው ይብላኝ እንጂ አንቺስ ሰው አታጪ
ይሻል ይሁን ብለሽ ከተነሳሽ አንቺ
እኔም ሸኝቻለሁ በይ ደህና ሰንብቺ
ይሻል ይሁን ብለሽ ከተነሳሽ አንቺ
እኔም ሸኝቻለሁ በይ ደህና ሰንብብቺ
የህልምሽ ሎተሪ ቅዠት ነው አይወጣም
ይባስ ይሁን እንጂ የተሻለ አይመጣም
ገንዘብ ከሰው በልጦ ከጠቀመሽ ላንቺ
አላስገድድሽም በይ ደህና ሰንብቺ
ገንዘብ ከሰው በልጦ ከጠቀመሽ ላንቺ
አላስገድድሽም በይ ደህና ሰንብቺ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists