Kishore Kumar Hits

Tsegaye Eshetu - Gelglegne lyrics

Artist: Tsegaye Eshetu

album: Best of Tsegaye Eshetu


እርግፍ አረግሽው ረሳሽው ልቤን ጎዳሽው
እርግፍ አረግሽው ገፋሽው ልቤን ጎዳሽው
ተስፋ አንዳልሰጠሽው ከመውደድሽ አሳነሽው
ተስፋ አንዳልሰጠሽው ፍቅርን ነስተሽ አበረርሽው
እርግፍ አረግሽው ጎዳሽው ልቤን ገፋሽው
እርግፍ አረግሽው ረሳሽው ልቤን ጎዳሽው
ተስፋ አንዳልሰጠሽው ከመውደድሽ አሳነሽው
ተስፋ አንዳልሰጠሽው ፍቅርን ነስተሽ አበረርሽው
ልጠይቅሽ ተጏዥ ነው ስንቅ የለው
ጏዝም የለው ጭኖታል ፈረሱን
ልብ አድርገሽ ይሄንን እንቆቅልሽ
በይ አስበሽ ድረሺበት መልሱን
ተጠይቀሽ መተንተን ካቃተሽ
ከከበደሽ የፍቅር ጨዋታው
ካላወቅሽው ካጣሽው ሚስጥሩን
ሀገር ስጪኝ እንግዲ እኔ ልፍታው
እድሜ ላንቺ ካሳብ ምን አጥቼ
ከሰጠሺኝ አስኪ ላውጠንጥነው
በይ ልንገርሽ ፈርሱም ነገርሽ
ስንቁም ፍቅርሽ ተጏዡም ልቤ ነው
በይ ልንገርሽ ፈርሱም ነገርሽ
ስንቁም ፍቅርሽ ተጏዡም ልቤ ነው
በይ ደና ሁኚ መቼም አይገባሽ የሰው ፍቅር
እንግዲ እኔም ካንቺ ማደሩ ሲያምረኝ ይቅር
በቃኝ አልኩኝ ስለሰለችኝ መጎትጎቱ
እስኪ ልየው ይሻለኝ እንደው መለየቱ
ወትሮም ላይቀናኝ ፍቅር ሰው ወድጄ
የቁም ስቃይ አየሁ በገዛ እጄ
ዛሬስ የነገር ኑሮ ሰለቸኝ
ያንታለ መረረኝ ያንታለ ገልግለኝ በቃ
ያንታለ ገልግለኝ ያንታለ መረረኝ አቅም የለኝ
ወትሮም ላይቀናኝ ፍቅር ሰው ወድጄ
የቁም ስቃይ አየሁ በገዛ እጄ
ተስፋ ቢስ ሆኖ መኖር ሰለቸኝ
ያንታለ መረረኝ ያንታለ ገልግለኝ በቃ
ያንታለ ገልግለኝ ያንታለ መረረኝ አቅም የለኝም
እርግፍ አረግሽው ረሳሽው ልቤን ጎዳሽው
እርግፍ አረግሽው ገፋሽው ልቤን ጎዳሽው
ተስፋ አንዳልሰጠሽው ከመውደድሽ አሳነሽው
ተስፋ አንዳልሰጠሽው ፍቅርን ነስተሽ አበረርሽው
ተወት አረግሽው ጎዳሽው ልቤን ጎፋሽው
ተወት አረግሽው ረሳሽው ልቤን ጎዳሽው
ተስፋ አንዳልሰጠሽው ከመውደድሽ አሳነሽው
ተስፋ አንዳልሰጠሽው ፍቅርን ነስተሽ አበረርሽው
የሚገባሽ የሚሰማሽ መስሎኝ
በቁም ነገር ስተርክ መዉደዴን
ላይሆንልኝ ጊዜዬን ጨረስኩት
ስዘረግፍ አውጥቼው የሆዴን
የሰው ነገር ትረጅያለሽ እያልኩ
የሃሳቤን እየዘረዘርኩኝ
ስለ ፍቅር የማውቀውን ያህል
በምሳሌ ብዙ ተናገርኩ
አወጋሁት ተጫወትኩ እስካሁን ተናገርኩት አለቀ ነገሬ
በኔ በኩል ልሂድ ጨርሻለው አሰናብቺኝ ሩቅ ነው ሀገሬ
በኔ በኩል ልሂድ ጨርሻለው አይምሽብኝ ሩቅ ነው ሀገሬ
በይ ደና ሁኚ መቼም አይገባሽ የሰው ፍቅር
እንግዲ እኔም ካንቺ ማደሩ ሲያምረኝ ይቅር
በቃኝ አልኩ ስለሰለቸኝ መጎትጎቱ
እስኪ ልየው ይሻለኝ እንደው መለየቱ
ወትሮም ላይቀናኝ ፍቅር ሰው ወድጄ
የቁም ስቃይ አየሁ በገዛ እጄ
ዛሬስ የነገር ኑሮ ሰለቸኝ
ያንታለ መረረኝ ያንታለ ገልግለኝ በቃ
ያንታለ ገልግለኝ ያንታለ መረረኝ አቅምም የለኝ
ወትሮም ላይቀናኝ ፍቅር ሰው ወድጄ
የቁም ስቃይ አየሁ በገዛ እጄ
ተስፋ ቢስ ሆኖ መኖር ሰለቸኝ
ያንታለ መረረኝ ያንታለ ገልግለኝ በቃ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists