ዛሬ ነዉ አለም ደስታችሁ ዛሬ ነዉ አለም ደስታችሁ ኦሆሆ የሁለታችሁ
ዛሬ ነዉ አለም ደስታችሁ ዛሬ ነዉ አለም ደስታችሁ ኦሆሆ የሁለታችሁ
የዉብ ናት የዉብ አበባ የዉብ ናት የዉብ አበባ ኦሆሆ የዉብ አበባ
የዉብ ናት የዉብ አበባ የዉብ ናት የዉብ አበባ ኦሆሆ የዉብ አበባ
ሙሽሪት እይዋት ተዉባ የዉብ ናት የዉብ አበባ ኦሆሆ የዉብ አበባ
የዉብ ናት የዉብ አበባ የዉብ ናት የዉብ አበባ ኦሆሆ የዉብ አበባ
ዛሬ ነዉ ሙሽራ አለምህ ዛሬ ነዉ ሙሽራ አለምህ ኦሆሆ ሙሽራ አለምህ
ዛሬ ነዉ ሙሽራ አለምህ ዛሬ ነዉ ሙሽራ አለምህ ኦሆሆ ሙሽራ አለምህ
ለዚህ ወግ በመታደልህ ዛሬ ነዉ ሙሽራ አለምህ ኦሆሆ ሙሽራ አለምህ
ዛሬ ነዉ ሙሽራ አለምህ ዛሬ ነዉ ሙሽራ አለምህ ኦሆሆ ሙሽራ አለምህ
ኩራት ነዉ ለእናት ለአባትሽ ኩራት ነዉ ለእናት ለአባትሽ ኦሆሆ ለእናት ለአባትሽ
ኩራት ነዉ ለእናት ለአባትሽ ኩራት ነዉ ለእናት ለአባትሽ ኦሆሆ ለእናት ለአባትሽ
በክብር በወግ ማግባትሽ ኩራት ነዉ ለእናት ለአባትሽ ኦሆሆ ለእናት ለአባትሽ
ኩራት ነዉ ለእናት ለአባትሽ ኩራት ነዉ ለእናት ለአባትሽ ኦሆሆ ለእናት ለአባትሽ
ድብልቅልቅ ይበል ጭፈራዉ ድብልቅልቅ ይበል ጭፈራዉ ኦሆሆ ይበል ጭፈራዉ
ድብልቅልቅ ይበል ጭፈራዉ ድብልቅልቅ ይበል ጭፈራዉ ኦሆሆ ይበል ጭፈራዉ
ሊወስዳት መቷል ሙሽራዉ ድብልቅልቅ ይበል ጭፈራዉ ኦሆሆ ይበል ጭፈራዉ
ድብልቅልቅ ይበል ጭፈራዉ
ድብልቅልቅ ይበል ጭፈራዉ ኦሆሆ ይበል ጭፈራዉ
ይገርማል ይደንቃል አቤት የአምላክ ስራ የእግዝአብሔር ስራ
ይገርማል ይደንቃል አቤት የአምላክ ስራ የእግዝአብሔር ስራ
ሙሽሪትን እይዋት ሙሽሪትን እይዋት ከሙሹራዉ ጋራ ሙሽሪትን እይዋት ሙሽሪትን እይዋት ከሙሹራዉ ጋራ
ሁለቱም በፍቅር በአንድ ያቆራኛቸዉ (የእግዝአብሔር ስራ)
በትዳር ሰንሰለት ያስተሳሰራቸዉ (የእግዝአብሔር ስራ)
እሷን ለሱ መርጦ እሱን ለሷ መርጦ የት አገናኛቸዉ
እሷን ለሱ መርጦ እሱን ለሷ መርጦ የት አገናኛቸዉ
እዩልኝ ዉበቷን ሙሽሪቷን
እዩልኝ ዉበቷን ሙሽሪቷን
እዩልኝ ግርማዉን ሙሽራዉን
እዩልኝ ግርማዉን ሙሽራዉን
ሱፉን ግጥም አርጐ እዩልኝ ግርማዉን
እዩልኝ ግርማዉን ሙሽራዉን
ሚዜዎቹ መሃል እዩልኝ ግርማዉን እዩልኝ ግርማዉን ሙሽራዉን የሙሽራዉ ዉበት
እዩልኝ ግርማዉን እዩልኝ ግርማዉን ሙሽራዉን ከኮኮብ ያበራል እዩልኝ ግርማዉን እዩልኝ ግርማዉን ሙሽራዉን
እዩልኝ ዉበቷን ሙሽሪቷን
እዩልኝ ዉበቷን ሙሽሪቷን
እዩልኝ ግርማዉን ሙሽራዉን
እዩልኝ ግርማዉን ሙሽራዉን
ነይ ሙሽሪት ነይ ሙሽሪት ነይ ሙሽሪት ነይ ና ሙሽራዉ ና
ሙሽራዉ ና ሙሽራዉ ና ነይ ሙሽሪት ነይ ሙሽሪት ነይ ሙሽሪት ነይ
ሙሽሪት ሙሽሪት ስትታይ ተዉባ
አበባስ ማለት የሷን ድንቅ ዉበት ሙሽሪት ሙሽሪት ስትታይ ተዉባ አበባስ ማለት የሷን ድንቅ ዉበት
ሙሽሪት ሙሽሪት መታለች ተዉባ አበባስ ማለት የሷን ድንቅ ዉበት
ሙሽሪት ሙሽሪት መታለች ተዉባ አበባስ ማለት የሷን ድንቅ ዉበት
ሙሽሪት ስትወጣ ሙሽሪት ሙሽሪት በቬሎ ተዉባ ሙሽሪት ዉቢቷ ሙሽሪት ስትወጣ ሙሽሪት
ሙሽሪት ከባን ደርባ ሙሽሪት ዉቢቷ አበባ ልትቀስም ሙሽሪት ሙሽሪት በራ መጣች ንቧ ሙሽሪት ዉበቷ
እዉነትም ሙሽሪት ሙሽሪት ሙሽሪት አበባ መስላለች ሙሽሪት ዉቢቷ ሲያይዋትም ሙሽሪት ሙሽሪት
ሙሽሪት አበባ መስላለች ሙሽሪት ዉቢቷ እንኳን የሰዉ አይ ሙሽሪት ሙሽሪት ንብ ታሳስታለች ሙሽሪት ዉቢቷ
ሙሽሪት ሙሽሪት መታለች ተዉባ አበባስ ማለት የአንቺን ድንቅ ዉበት ሙሽሪት ሙሽሪት መታለች ተዉባ
አበባስ ማለት የአንቺን ድንቅ ዉበት
ሙሽሪት ዉብ አበባ ሙሽሪት ዉብ አበባ ድረሽልኝ ሆዴ ባባ
ሙሽሪት ዉብ አበባ ሙሽሪት ዉብ አበባ ድረሽለት ሆዴ ባባ
ሙሽራዬ ሆይ ሙሽራዬ ሆይ ሙሽራዬ ሆይ መሄድሽ ነዉ ወይ ሙሽሪት እርቃ ሙሽሪት እርቃ
ሙሽሪት እርቃ መሄዷ ነዉ በቃ ሙሽራዬ ሆይ ሙሽራዬ ሆይ ሙሽራዬ ሆይ መሄድሽ ነዉ ወይ
በቃ ሄደች ሄደች እራሷን ልትችል በቃ ሄደች ሄደች እራሷን ልትችል
ልጅነቷ ቀርቶ እሷም ልጄን ልትል ልጅነቷ ቀርቶ እሷም ልጄን ልትል
ይሄዉ ሄደች ሄደች ልትባል ወይዘሮ ይሄዉ ሄደች ሄደች ልትባል ወይዘሮ ሚስት ሆና
ልታዬዉ የትዳርን ኑሮ ሚስት ሆና ልታዬዉ የትዳርን ኑሮ ሙሽራዬ ሆይ ሙሽራዬ ሆይ
ሙሽራዬ ሆይ መሄድሽ ነዉ ወይ ሙሽራዬ ሆይ ሙሽራዬ ሆይ ሙሽራዬ ሆይ መሄድሽ ነዉ ወይ
ሸኚ የለሽም ወይ የለሽም
ሸኚ የለሽም ወይ የለሽም
ሸኚ የለሽም ወይ የለሽም
ሸኚ የለሽም ወይ የለሽም
ዉብ አበባ አበባ የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ ዉብ አበባ አበባ የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ
በእንክብካቤ ነዉ የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ ሙሽሪት ስታድግ የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ
ተንከባክበህ ያዛት የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ እንዳትጠወልግ የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ
በእናቷም በአባቷም የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ ከነ አፈጣጠሯ የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ
ቆንጆ የቆንጆ ልጅ የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ አበባ ነዉ ዘሯ የአይኔ አበባ አበባ የአይኔ አበባ
እንደማተባችሁ እንደ አንገታችሁ ክር እንደማተባችሁ እንደ አንገታችሁ ክር ትዳራችሁ ይፅና ፍቅራችሁ ይጠንክር
እንግዲህ ሙሽሮች አንድ አካል ሆናችሁ እስከመጨሻ አንድ አምሳል ሆናችሁ ከሞት በቀር ሌላ ምንም አይለያችሁ
ሆይ መላ ነሽ አሉ ሆይ መላ እንደዉ መላ መላ
ሆይ መላ ነሽ አሉ ሆይ መላ እንደዉ መላ መላ ሆይ መላ እንቅፋት አይጠፋም እንደዉ መላ መላ ሆይ መላ
በትዳር ጐዳና እንደዉ መላ መላ ሆይ መላ በዘዴ መልሺዉ
እንደዉ መላ መላ ሆይ መላ ሁሉንም ፈተና እንደዉ መላ መላ
ሆይ መላ የቤትሽ ምሰሶ እንደዉ መላ መላ ሆይ መላ ማገሩ እንዳይላላ እንደዉ መላ መላ
ሆይ መላ እንደሚሆን አርጊዉ እንደዉ መላ መላ ሆይ መላ በመላ በመላ እንደዉ መላ መላ
እንግዲ ሙሽሪት እንግዲ ሙሽራ እንግዲ ሙሽሪት እንግዲ ሙሽራ ሁለታችሁ ናችሁ የቤታችሁ ጣራ
በአንድ ወገን እንዳይዘም የቤቱ ማዕዘን በአንዱ
እንዳያጋድል የቤቱ ባዕዘን ትዳር የእኩል ቤት ነዉ ይኑር መተዛዘን
ደስ አይሉም ወይ እሰይ እሰይ
አያስቀኑም ወይ እንበል እሰይ ሙሽሪት ሙሽራዉ እሰይ እሰይ ሆነዉ አንድ ላይ እንበል እሰይ
የጀመሩት ትዳር እሰይ እሰይ አብሮ እንዲያዘልቃቸዉ እንበል እሰይ
አይለያችሁ ብለን እሰይ እሰይ እስቲ እንመርቃቸዉ እነበል እሰይ
እንደማተባችሁ እንደ አንገታችሁ ክር እንደማተባችሁ እንደ አንገታችሁ ክር ትዳራችሁ ይፅና ፍቅራችሁ ይጠንክር
እንግዲህ ሙሽሮች አንድ አካል ሆናችሁ እስከመጨሻ አንድ አምሳል ሆናችሁ ከሞት በቀር ሌላ ምንም አይለያችሁ
እህህ የጋብቻችሁ ቀን እሰይ እሰይ እህ እንዲ እንደደመቀ እንበል
እሰይ እህ ያርገዉ ኑሯችሁን እሰይ እሰይ እህ ያማረ የሞቀ እንበል እሰይ
እህ እንዲ እንዳማረበት እሰይ እሰይ ጋብቻ ሰርጋችሁ እንበል እሰይ
እህ ደስታ የሞላበት እሰይ እሰይ እህ ትዳር ያርግላችሁ እንበል እሰይ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist