Kishore Kumar Hits

Tsegaye Eshetu - Man Anchin Yiketelal lyrics

Artist: Tsegaye Eshetu

album: Nigat


እኖራለሁ ወድጄሽ
ወሰንሽ ፍቅር ነው ፍቅር እንዴት ይለካል
እስቲ አንቺን አስረስቶ ማን አንቺን ይተካል
እኖራለሁ ወድጄሽ
መውደድሽ ስንቅ ነው በሩቅም ያስመካል
እስቲ አንቺን አስረስቶ ማን አንቺን ይተካል

ፍቅርሽ ጣፋጭ ቃናው ከቶ አይለወጥም
ልቤን አሳልፌ ለማንም አልሰጥም
አንቺን የሚያስጥል ሰው ቢሰለፍ አልመርጥም
እመኚኝ ይሔንቃል እምነቴን አልሽጥም
ሰቀቀኔ ካንቺጋ ምን አጥቼ
ወዴት ልሂድ አንችን ትቼ
ሰቀቀኔ የመውደድ ሰቀቀኔ
ካይኔ አልጣሽ ኑሪ ለኔ
ደፋ ቀና እያልሽልኝ እየለፋሽ
እንዴት ብዬ ነው ውዴ የማስከፋሽ
የማልጠላሽ ነሽ የፍቅር እመቤቴ
እንድረሳሽ አልፈቅድም በሒወቴ

እኖራለሁ ወድጄሽ
ወሰንሽ ፍቅር ነው ፍቅር እንዴት ይለካል
እስቲ አንቺን አስረስቶ ማን አንቺን ይተካል
እኖራለሁ ወድጄሽ
መውደድሽ ስንቅ ነው በሩቅም ያስመካል
እስቲ አንቺን አስረስቶ ማን አንቺን ይተካል

ሰው ሆነሽ ተፈጥረሽ በዚህ ምድር ሳለሽ
ለኔጂ ለራስሽ መች ኖረሽ ታውቂያለሽ
የልቤን ትርታ ቀድመሽ ትሰሚያለሽ
ተፈጥሮሽ ልዩ ነው አንቺስ ትገርሚያለሽ
ሰቀቀኔ ካንቺጋ ምን አጥቼ
ወዴት ልሂድ አንችን ትቼ
ሰቀቀኔ የመውደድ ሰቀቀኔ
ካይኔ አልጣሽ ኑሪ ለኔ
ደፋ ቀና እያልሽልኝ እየለፋሽ
እንዴት ብዬ ነው ውዴ የማስከፋሽ
የማልጠላሽ ነሽ የፍቅር እመቤቴ
እንድረሳሽ አልፈቅድም በሒወቴ
ደፋ ቀና እያልሽልኝ እየለፋሽ
እንዴት ብዬ ነው ውዴ የማስከፋሽ
የማልጠላሽ ነሽ የፍቅር እመቤቴ
እንድረሳሽ አልፈቅድም በሒወቴ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists