Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Andiken lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Andiken


አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
ተስፋ አይጣልም አታመንታ በጣም
ካገር ልጅ በስተቀር ሌላው አያዋጣም
ይመስልሃል እንጅ ለጊዜው ለወቅቱ
ሁሉም ዞሮ መግቢያ ሃገሩ ነው ቤቱ
ሁሉም ዞሮ መግቢያ ሃገሩ ነው ቤቱ

በስደት ኑሮ ላይ ዘመድ አዝማድ ወሬ እንኳን መጥቶ መርዶ
(እንኳን መጥቶ መርዶ)
በሰው ሃገር መሬት ብሶት ያመነጨው እንባ መቼ ገዶ
(እንባ መቼ ገዶ)
መብላት መጠጣቱ ሃዘን ደስታውም የሚያምረው ባገር ነው
(የሚያምረው ባገር ነው)
ሆድ ይቻለው እንጅ ወደድንም ጠላንም የሰው ቤት የሰው ነው
(የሰው ቤት የሰው ነው)
ያልፍልኛል ብሎ ያ ሁሉ ወገኔ ካገሩ ተሰድዶ
(ካገሩ ተሰድዶ)
የተገላቢጦሽ የታቹ ላይ ወጥቶ የላዩ ታች ወርዶ
(የላዩ ታች ወርዶ)
ወገኔ ያገር ልጅ ወገኔ ያገር ሰው
ለሚያልፍ ቀን ብለህ ሆድክን አታስብሰው
ካገርህ ልጅ ጋራ ባገርህ መኪና
መደሰት አይቀርም ይቺ ቀን ታልፍና
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን

ተስፋ አይጣልም አታመንታ በጣም
ካገር ልጅ በስተቀር ሌላው አያዋጣም
ይመስልሃል እንጅ ለጊዜው ለወቅቱ
ሁሉም ዞሮ መግቢያ ሃገሩ ነው ቤቱ
ሁሉም ዞሮ መግቢያ ሃገሩ ነው ቤቱ

ሲታመሙ አስታሞ ሲታሰር ጠይቆ ሲከፋ ሚያፅናና
(ሲከፋ ሚያፅናና)
ወዲያ ወዲህ ቢሉ ማን እንደ ሃገር ልጅ ከቶስ የት አለና?
(ከቶስ የት አለና?)
በያገሩ ጋርዶ የውስጡን አምቆ ሲቃይ ሲያይ መከራ
(ሲቃይ ሲያይ መከራ)
አወይ ያገሬ ሰው ማን ሰምቶ ይመልስ ማን ስላንተ ያውራ?
(ማን ስለሱ ያውራ?)
ብቸኝነት ነግሶ ዛሬ ብትከፋ ሃዘንህ ቢፀና
(ሃዘንህ ቢፀና)
የትናንቱን መልካም የመጪውን ደስታ አስበህ ተፅናና
(አስበህ ተፅናና)
ወገኔ ያገር ልጅ ወገኔ ያገር ሰው
ለሚያልፍ ቀን ብለህ ሆድክን አታስብሰው
ካገርህ ልጅ ጋራ ባገርህ መኪና
መደሰት አይቀርም ይቺ ቀን ታልፍና
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
አንድ ቀን አንድ ቀን
አንድ ቀን አይቀርም አንድ ቀን
አንድ ቀን አንድ ቀን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists