Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Maldesh lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Andiken


ማልደሽ ድረሺ ለኔ ድረሺ ለኔ
ናፍቆት ይጠብቅሻል ወዳጅሽ አይኔ
ባንቺ ምክንያት ይብቃ እንጂ መባከኔ
ባንቺ ምክንያት ይብቃ እንጂ መባከኔ
ማልደሽ ድረሺ ለኔ ድረሺ ለኔ
ናፍቆት ይጠብቅሻል ወዳጅሽ አይኔ
ባንቺ ምክንያት ይብቃ እንጂ መባከኔ
ባንቺ ምክንያት ይብቃ እንጂ መባከኔ
እንድትመለሺ በሰላም በጤና
መርቄ ሸኝቼሽ አሲዤሽ ጎዳና
ስጠብቅሽ ውዬ ማዶ ማዶ እያየው
ቀን መሽቶ ነጋብኝ እየተሰቃየው
አካሌ ደከመ መፈሴ ተረታ
በምሽቱ ጭንቀት በቀኑ ትዝታ
ክፍት ይለኛል ሲስቁ አልስቅም
እንደ ዘንድሮ ጉድ ሆኜ አላውቅም
ልቤ ግራ እንደገባው ቀልቤም እንደተጉላላ
ባስብ ባስብ ባልመው ሳላገኝለት መላ
ቀኑ ቀን ወልዶ ሳምንት ሆኖኛል
እኔስ ጨነቀኝ ምን ይሻለኛል
ልቤ ግራ እንደገባው ቀልቤም እንደተጉላላ
ባስብ ባስብ ባልመው ሳላገኝለት መላ
ቀኑ ቀን ወልዶ ሳምንት ሆኖኛል
እኔስ ጨነቀኝ ምን ይሻለኛል
ማልደሽ ማልደሽ ነይማ
ማልደሽ ማልደሽ ነይማ
ማልደሽ ድረሺ ለኔ ድረሺ ለኔ
ናፍቆት ይጠብቅሻል ወዳጅሽ አይኔ
ባንቺ ምክንያት ይብቃ እንጂ መባከኔ
ባንቺ ምክንያት ይብቃ እንጂ መባከኔ
ማልደሽ ድረሺ ለኔ ድረሺ ለኔ
ናፍቆት ይጠብቅሻል ወዳጅሽ አይኔ
ባንቺ ምክንያት ይብቃ እንጂ መባከኔ
ባንቺ ምክንያት ይብቃ እንጂ መባከኔ
ከወጪ ወራጁ ከሚመላለሰው
አንድ አፅናኝ ቢጠፋ አየኃት የሚል ሰው
እናቱን እንዳጣ ህፃን እየባባው
መኖር ጀምሬያለው ጠዋት ማታ እያነባው
አድራለው ፈጥቼ አልተኛም እንደሰው
ሀሳብ ህሊናዬ እየቀሰቀሰው
ክፍት ይለኛል ሲስቁ አልስቅም
እንደ ዘንድሮ ጉድ ሆኜ አላውቅም
ነፍሴ ግራ እንደገባት ስጋዬ እንደተጉላላ
ባስብ ባስብ ባልመው ሳላገኝለት መላ
ሳምንቱ በሮ ወሩም አለፈ
ድምፅሽም ጠፋ ግዜው ከነፈ
ነፍሴ ግራ እንደገባት ስጋዬ እንደተጉላላ
ባስብ ባስብ ባልመው ሳላገኝለት መላ
ሳምንቱ በሮ ወሩም አለፈ
ድምፅሽም ጠፋ ግዜው ከነፈ
ማልደሽ ማልደሽ ነይማ
ማልደሽ ማልደሽ ነይማ
ማልደሽ ማልደሽ ነይማ
ማልደሽ ማልደሽ ነይማ
ማልደሽ ማልደሽ ነይማ
ማልደሽ ማልደሽ ነይማ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists