Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Anchin New (You're The One) lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Anchin New (You Are The One)


ልቤን እስጨንቆት ፍቅሯ መላ ኣሳጥቶት
ታስሯል በናፍቆቷ እርዳታ ተስኖት
መድረኩ ያለሷ እይደምቅም
እቻ የሚወዳደር አላውቅም
ልቤን እስጨንቆት ፍቅሯ መላ ኣሳጥቶት
ታስሯል በናፍቆቷ እርዳታ ተስኖት
መድረኩ ያለሷ እይደምቅም
እቻ የሚወዳደር አላውቅም
ዳሌ ሲኮራ ሲንደላቀቅ
ምጥኑ ሽንጥሽ ሲያምር ሲራቀቅ
እዩኝ ይሚለው ባትሽ ውበቱ
ልቤን ወሰደው ከቋሚ ቤቱ
አንቺን ነው ልቤ ሚለው
ተረጂልኝ ፍቅሬ ምነው
አንቺን ነው ልቤ ሚለው
ተረጂልኝ ፍቅሬ ምነው
ደረትሽ ጮራ ሲፈነጥቅ
ጥርስሽ ሲያበራ ልቤ ሲመጥቅ
ባትሽ ሲወራጭ ለጨዋታ
ይናፍቀኛል ሁል ጊዜ ማታ
አንቺን ነው ልቤ ሚለው
ተረጂልኝ ፍቅሬ ምነው
አንቺን ነው ልቤ ሚለው
ተረጂልኝ ፍቅሬ ምነው
ልቤን እስጨንቆት ፍቅሯ መላ ኣሳጥቶት
ታስሯል በናፍቆቷ እርዳታ ተስኖት
መድረኩ ያለሷ እይደምቅም
መድረኩ ያለሷ እይደምቅም
እቻ የሚወዳደር አላውቅም
አይንሽ ሲያበራ ለመድረኩ
የመግለጫ ቃል ይጠፋል ልኩ
መለሎ ነሽ ሀረግ ዘንጋታ
ልደንስ ካንቺ አልሻም ፋታ
አንቺን ነው ልቤ ሚለው
ተረጂልኝ ፍቅሬ ምነው
አንቺን ነው ልቤ ሚለው
ተረጂልኝ ፍቅሬ ምነው
አንቺ የቆንጆ ዳርቻ ነሽ
ተቀመጭ የልቤ ንግሥት ሆነሽ
መደረኩን ለሷ አርጉላት ሰፋ
እንዳትነካ እንዳትከፋ
አንቺን ነው ልቤ ሚለው
ተረጂልኝ ፍቅሬ ምነው
አንቺን ነው ልቤ ሚለው
ተረጂልኝ ፍቅሬ ምነው
ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ
እጃችሁን ወደላይ ወደላይ ወደላይ
ከፍ አርጉት
ትምጣ ትታይ ትሽቀርቀር
ውብቷን አድንቁት
ሁለት ወደ ግራ ወደ ግራ
ሁለት ወደ ቀኝ ወደ ቀኝ
እናምሽ አንድ ላይ በፍቅር
ሳቅሽ ጨዋታሽ አይራቀኝ
ሁለት ወደ ግራ ወደ ግራ
ሁለት ወደ ቀኝ ወደ ቀኝ
እናምሽ አንድ ላይ በፍቅር
ሳቅሽ ጨዋታሽ አይራቀኝ
ከፍ ከፍ ከፍ
ከፍ ከፍ ከፍ
ወደ ግራ ወደ ቀኝ
እናምሽ አንድ ላይ ፍቅርሽ አይራቀኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists