Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Ayisemashim lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Anchin New (You Are The One)


አይሰማሽም አይታይሽም
ፍቅር ለሰጠሽ ምላሽ የለሽም
እኔ አንቺን ለኔ አርቄ አስቤ
ለምን ልጠቃ መውደድ ተርቤ
አይሰማሽም አይታይሽም
ፍቅር ለሰጠሽ ምላሽ የለሽም
እኔ አንቺን ለኔ አርቄ አስቤ
ለምን ልጠቃ መውደድ ተርቤ

ትዕግስቴን ከፍርሃት ብታይ ከግዴታ
ትቆጥሪው ጀመረ ሳትቆጠሪ ውለታ
አልታይሽ ካለ መጎዳቴ ላንቺ
ያዝሽውን መንገድ ጨርቅ ያርግልሽ በርቺ
መረዳዳት ካቃተን ይብቃን ይቅር ግዴለም
ሰቶ የማይቀበል በዚች አለም ላይ የለም
መታመኔን በቸርኩኝ ጭንቀት ማትረፌ ምነው?
የተፈጠርነው በእርግጥ ሁላችንም ከሰው ነው
መረዳዳት ካቃተን ይብቃን ይቅር ግዴለም
ሰርቶ የማይቀበል በዚች አለም ላይ የለም
መታመኔን በቸርኩኝ ጭንቀት ማትረፌ ምነው?
የተፈጠርነው በእርግጥ ሁላችንም ከሰው ነው
አይሰማሽም አይታይሽም
ፍቅር ለሰጠሽ ምላሽ የለሽም
አይሰማሽም አይታይሽም
ፍቅር ለሰጠሽ ምላሽ የለሽም

አይሰማሽም አይታይሽም
ፍቅር ለሰጠሽ ምላሽ የለሽም
እኔ አንቺን ለኔ አርቄ አስቤ
ለምን ልጠቃ መውደድ ተርቤ
አይሰማሽም አይታይሽም
ፍቅር ለሰጠሽ ምላሽ የለሽም
እኔ አንቺን ለኔ አርቄ አስቤ
ለምን ልጠቃ መውደድ ተርቤ
እዘልቃለሁ ብዬ በደልሽን ብሸከም
በሽታ ሰጠሽኝ ከቶ ማይታከም
ካልተጨነቅሽልኝ እኔ አልጨነቅም
ላያዘልቀኝ ፀሎት ትካዜ አልሰንቅም
መኖር ራስን ወዶ ለራስ ብቻ ተጨንቆ
ከሰው ይለያል እንጂ ውጤት የለውም ዘልቆ
መውደድ መስጠት መቀበል የተሰጠ ፀጋ ነው
ላንቺ ምቾት መጣሬ ማይሰማሽ ለምን ነው?
መኖር ራስን ወድዶ ለራስ ብቻ ተጨንቆ
ከሰው ይለያል እንጂ ውጤት የለውም ዘልቆ
መውደድ መስጠት መቀበል የተሰጠ ፀጋ ነው
ላንቺ ምቾት መጣሬ ማይሰማሽ ለምን ነው?
አይሰማሽም አይታይሽም
ፍቅር ለሰጠሽ ምላሽ የለሽም
አይሰማሽም አይታይሽም
ፍቅር ለሰጠሽ ምላሽ የለሽም
ተረጂልኝ ባክሽን እዘኝልኝ ግዴለም
ያዋተተኝ እናድንቺ በዚች አለም ላይ የለም
መኖር ያላንቺ ከብዶኝ ግራ ገባኝ እኔማ
እንዲቀለኝ ጭንቀቴ ለአንድ አፍታ ነይማ
ለአንድ አፍታ ነይማ
ለአንድ አፍታ ነይማ
ለአንድ አፍታ ነይማ ነይማ
ለአንድ አፍታ ነይማ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists