Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Keremela lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Anchin New (You Are The One)


ፈካች ጨረቃ
ኮኮብ ደመቀ
ጉም ለብሶ ጀምበር
ካድማስ ራቀ
መስኩም ጨላልሞ
ላይን ይዞ ማታ
እጨነቃለሁ
ባንቺው ትዝታ
የልቤ ራብ ነሽ
አታሪፊም ካይኔ
ጭንቅ ይለኛል
ሳጣሽ ከጎኔ
ሰማዩ ጠርቶ
ሌቱ እስኪነጋ
አስብሻለሁ
ተኝቼ ካልጋ
ናፍቆቴ ሳይወጣ
አይቼ ሳልጠግብሽ
ደመና አለበሰሽ
ደረሰ መሄጃሽ
ለምን ይሆን ጊዜው
የሚገሰገሰው
ቀኑ ደቂቃ ነው ለተዋደደ ሰው
ደመናው ገፎ
ጎህ ሲቀድ ሰማይ
እጨነቃለሁ
አይንሽን እስካይ
ከላዬ መች ያርፍልኛል
ሲመሽ ሲነጋ
አንቺን ይለኛል
ዉቤ ዉቤ
ከረሜላ
ቤላ ቤላ
ከረመላ ውቤ
ዉቤ ዉቤ
ከረሜላ
ቤላ ቤላ
ከረመላ ውቤ
(ሙዚቃ)
ፈካች ጨረቃ
ኮኮብ ደመቀ
ጉም ለብሶ ጀምበር
ካድማስ ራቀ
መስኩም ጨላልሞ
ላይን ይዞ ማታ
እጨነቃለሁ
ባንቺው ትዝታ
የልቤ ራብ ነሽ
አታሪፊም ካይኔ
ጭንቅ ይለኛል
ሳጣሽ ከጎኔ
ሰማዩ ጠርቶ
ሌቱ እስኪነጋ
አስብሻለሁ
ተኝቼ ካልጋ
ያይን አሰባበረሽ
የጥርስሽ ንጣቱ
ፈገግታሽን ያየ
አይፀናም አንጀቱ
በማለዳው ቀርቶ
እልፍኝ ያልቀለሰው
ይሸፍታል ልቡ
ካህን, የቆረበ ሰው
ሁለመናሽ እንቁ
እንከንም የለሽ
ልቤን ማርኮታል
የሰራ አካልሽ
የማትሰለች የማር ወለላ
ከንፈርሽ ጣፋጭ
ነው ከረሜላ
ዉቤ ዉቤ
ከረሜላ
ቤላ ቤላ
ከረሜላ ውቤ
ዉቤ ዉቤ
ከረሜላ
ቤላ ቤላ
ከረሜላ ውቤ
ዉቤ ዉቤ
ዉቤ ዉቤ
ቤላ ቤላ
ዉቤ ዉቤ
ቤላ ቤላ
ቤላ ቤላ
ቤላ ቤላ
ዉቤ ዉቤ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists