Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Derbabaye lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Lottery


እቴ ወሸባ እባክሽ እቴ ወሸባ
የማነሽ ቀዘባ
ንገሪኝ አንቺ አይነ ሌባ
እቴ ወሸባ ደርባባዬ ብዬሽ
ተወራርጄብሽ ይኸው ተሸነፍኩልሽ
ተፈጥሮሽን እያስተዋልኩት ብቻዬን
የአምላክ ፀጋ ለኔም ደረሰኝ ተመስገን
ሰው አይንካሽ ጭራሽ ባያዩሽ ደስ ይለኛል
ድንቅ ውበትሽን እንዳሞግሰው ተሰጥቶኛል
ነጩ ጥርስሽ የጥቅምት እንኩብ የመሰለው
የተስፋ እና የመደሰቻዬ ምንጭ ነው
የኔ ዞማ ባንቺው ልኩራራ ልደሰት
አይጠገብ የእግዜር ተፈጥሮ ድንቅ ውበት
የኔ ፍቅር የኔ ዞማ
ቀማኋቸው ሳልቀማ
ስንቱ ጀግና ሞክሮኝ
ዘራፍ ላንቺ አሰኘኝ
ልቤም ወዶሽ እምቢ እያለ
ድንቅ ውበትሽን ተከተለ
ምድረ ጎበዝ ቢቋምጥም
አንቺን መሳይ እንዴት ልስጥ
እንዲህ ነው ቁንጅና ውበት እስካማረ
ጎድሎ መፈጠሩስ ጭራሹን በቀረ
ይታደላሉ እንጂ አይታገሉትም
ተፈጥሮ የሰጠው ቦታውን አይስትም
አንቺዬ የፍቅር እንግዳ
ተቀመጭ ከልቤ ጓዳ
ፍቅሬን አስተናግዳለሁ
በጣሙን ወድጄሻለሁ
አንቺዬ የፍቅር እንግዳ
ተቀመጭ ከልቤ ጓዳ
ፍቅሬን አስተናግዳለሁ
በጣሙን ወድጄሻለሁ
እቴ ወሸባ እባክሽ እቴ ወሸባ
የማነሽ ቀዘባ
ንገሪኝ አንቺ አይነ ሌባ
እቴ ወሸባ ደርባባዬ ብዬሽ
ተወራርጄብሽ ይኸው ተሸነፍኩልሽ
ትኩር ብዬ ስመለከትሽ በትካዜ
ሰውነቴን ደስታ ተሰማው ባ'ንድ ጊዜ
ከሴቶቹ ለብቻ አድርጎ የፈጠረሽ
አለኝታዬ የምኮራብሽ ለኔ አንቺው ነሽ
እንደሰት ቤታችን ይሙቅ በጨዋታ
ዝምታሽን ከቶ አልወደውም የኔ አለኝታ
ከነጓዝሽ ፍቅርሽን ጫኚው በአካላቴ
ስሩን ሰዶ ነብሴም ይደሰት ሰውነቴ
የኔ ፍቅር የኔ ዞማ
ቀማኋቸው ሳልቀማ
ስንቱ ጀግና ሞክሮኝ
ዘራፍ ላንቺ አሰኘኝ
ልቤም ወዶሽ እምቢ እያለ
ድንቅ ውበትሽን ተከተለ
ምድረ ጎበዝ ቢቋምጥም
አንቺን መሳይ እንዴት ልስጥ
የማትሰለቺ ሁል ጊዜ ጣፋጭ
ቁንጭሽ መስታወት ነው የሚያብለጨልጭ
ከላይ እና ከታች ውበት የታለሽ
ምንም ያልጎደለሽ ውብ እመቤት ነሽ
ደርባባ ቆንጆ ተፈጥሮ
ሁሉን ሰጥቶ አሳምሮ
ዘራፍ ላንቺ አልኩልሽ
ውብ እመቤት አንቺው ነሽ
ደርባባ ቆንጆ ተፈጥሮ
ሁሉን ሰጥቶ አሳምሮ
ዘራፍ ላንቺ አልኩልሽ
ውብ እመቤት አንቺው ነሽ
አንቺዬ የፍቅር እንግዳ
ተቀመጭ ከልቤ ጓዳ
ፍቅሬን አስተናግዳለሁ
በጣሙን ወድጄሻለሁ
አንቺዬ የፍቅር እንግዳ
ተቀመጭ ከልቤ ጓዳ
ፍቅሬን አስተናግዳለሁ
በጣሙን ወድጄሻለሁ
ደርባባ ቆንጆ ተፈጥሮ
ሁሉን ሰጥቶ አሳምሮ
ዘራፍ ላንቺ አልኩልሽ
ውብ እመቤት አንቺው ነሽ
ደርባባ ቆንጆ ተፈጥሮ
ሁሉን ሰጥቶ አሳምሮ
ዘራፍ ላንቺ አልኩልሽ
ውብ እመቤት አንቺው ነሽ
አንቺዬ የፍቅር እንግዳ
ተቀመጭ ከልቤ ጓዳ
ፍቅሬን አስተናግዳለሁ
በጣሙን ወድጄሻለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists