Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Anchiw Dereshiligne lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Lottery


ፍቅር ወለላዬ ሆይ
መውደድ ወለላዬ ሆይ
ስጠብቅሽ ውዬ በጎዳናው ላይ
አይንሽን ሳላዬው ማደሬ ነው ወይ?
ፍቅር ወለላዬ ሆይ
መውደድ ወለላዬ ሆይ
ስጠብቅሽ ውዬ በጎዳናው ላይ
አይንሽን ሳላዬው ማደሬ ነው ወይ?

ተንገላታሁ አፍቅሬሽ በማጣቴ
እንዳይሆን ሆኖ ቀረ የኔማ ሰውነቴ
ውሎ እያ ደር በርትቷል የኔስ ጭንቄ
ሃሳብ ትካዜ ሆኖ የኔማ የቀን የሌሊት ስንቄ
ለተንከራተተው ለባዘነው አይኔ
ቀን መሽቶ እስከሚነጋ ለማያርፈው ጎኔ
ብታዝኝለት ምነው ለሚዎድሽ ልቤ
ካላንቺ ማን አለኝ አዛኝ ካጠገቤ

ሃሳብ ተሸክሜ ጭንቀትን ስገፋ
ናፍቆት ቅስሜን ሰብሮት አንገቴን ስደፋ
እ... ቴ ሳዝን ስከፋ
ምን ይጠቅምሻል ነይ ነይ የኔ ተሳፋ
እኔስ የለኝ የምልከው ሁነኛ አማላጅ
አንቺው ድረሽልኝ የልቤ ወዳጅ
እኔስ የለኝ የምልከው ሁነኛ አማላጅ
አንቺው ድረሽልኝ የልቤ ወዳጅ
ኦ... ሆ
ምቺ
ኦሆ

(ሙዚቃ)
ፍቅር ወለላዬ ሆይ
መውደድ ወለላዬ ሆይ
ስጠብቅሽ ውዬ በጎዳናው ላይ
አይንሽን ሳላዬው ማደሬ ነው ወይ?
ፍቅር ወለላዬ ሆይ
መውደድ ወለላዬ ሆይ
ስጠብቅሽ ውዬ በጎዳናው ላይ
አይንሽን ሳላዬው ማደሬ ነው ወይ?

አልከተል የሄድሽበትን መንገድ
ወይ አይቆርጥልኝ ልቤ
አይጣል ነው የኔስ መንደድ
ጭር ባለው በቀዘቀዘው ቤቴ
ሳስብሽ ውዬ አድራለሁ
በበድን አካላቴ
ምርኮኛው ቀልቤማ የኔነቱን ሽሮ
ካንቺው ጋር ተሰዷል
ክዶኛል ዘንድሮ
በብቸኝነቴ ጠላሁ መፈጠሬን
ወቀስኩት ረገምኩት
አመንኩት መፍቀሬን

ሃሳብ ተሸክሜ ጭንቀትን ስገፋ
ናፍቆት ቅስሜን ሰብሮት አንገቴን ስደፋ
እ... ቴ ሳዝን ስከፋ
ምን ይጠቅምሻል ነይ ነይ የኔ ተሳፋ
እኔስ የለኝ የምልከው ሁነኛ አማላጅ
አንቺው ድረሽልኝ የልቤ ወዳጅ
እኔስ የለኝ የምልከው ሁነኛ አማላጅ
አንቺው ድረሽልኝ የልቤ ወዳጅ
እኔስ የለኝ የምልከው ሁነኛ አማላጅ
አንቺው ድረሽልኝ የልቤ ወዳጅ
እኔስ የለኝ የምልከው ሁነኛ አማላጅ
አንቺው ድረሽልኝ የልቤ ወዳጅ
እኔስ የለኝ የምልከው ሁነኛ አማላጅ
አንቺው ድረሽልኝ የልቤ ወዳጅ
ኦ... ሆ
ምቺ
ኦሆ
ህዋ
ህዋ
ህዋ
ሶብ ሶብ
ሶብ ስብ
ህዋ
ሶብ ሶብ
ሶብ ስብ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists