Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Lijenetish Alfwal lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Lottery


ስሚኝ የኔ ህይወት እስኪ አድምጪኝ
ልጅነትሽ አልፏል አትሩጪ
ዛሬ አድገሻል ነብስ አውቀሻል
አልፏል ልጅነትሽ ማን ይጠብቅሻል
ለወግ ለማዕረግም ደርሰሻል
ከህይወት ትግል ገጥመሻል
አለምን መጋፈጥ ይሻልሻል
እንደልጅነትሽ ማን ያይሻል
አባጣ እና ጎርባጣው
መከራ እና ቁጣው
አለም የተውኔት ምድር ናት
ህይወት ጣፋጭም መራርም ናት
እንግዲህ ፍቅሬ ሆይ በዚህች አለም
ቀጥ ያለ መንገድ ህይወት የለም
የልጅነት ለዛ ቀለም
እንዳማረ ያለ የለም
አታላይ ናት ይቺ አለም
ከቤተሰቦችሽ እጅ ወጥተሽ
ትዳር ጎጆ መስረትሽ
ቀና መንገድ አበጅተሽ
ለመኖር ሞክሪ ጠንክረሽ
ህይወትን ታገያት በርትተሽ
ሁሉንም ችለሽው ታግሰሽ
ልጅነትሽ አልፏል ታውቂያለሽ
ዛሬ እኮ አድገሻል ትልቅ ሰው ነሽ
የኔ ህይወት ምክሬን ስሚኝ
በልብሽ ውስጥ ይሁን ቋሚ
ክፉ እና በጎውን እወቂ
አደራ ኪዳንን ጠብቂ
ከህይወት ልምዴ ላካፍልሽ
ፈረሱም ሜዳውም ያውልሽ
የልጅነት ለዛ ገደብ
እንዳማረ የሚኖር የለም
አታላይ ናት ይቺ አለም
አባጣ እና ጎርባጣው
መከራ እና ቁጣው
አለም የተውኔት ምድር ናት
ህይወት ጣፋጭም መራርም ናት
እንግዲህ ፍቅሬ ሆይ በዚህች አለም
ቀጥ ያለ መንገድ ህይወት የለም
የልጅነት ለዛ ቀለም
እንዳማረ ያለ የለም
አታላይ ናት ይቺ አለም
የኔ ህይወት ምክሬን ስሚኝ
በልብሽ ውስጥ ይሁን ቋሚ
ክፉ እና በጎውን እወቂ
አደራ ኪዳንን ጠብቂ
ከህይወት ልምዴ ላካፍልሽ
ፈረሱም ሜዳውም ያውልሽ
የልጅነት ለዛ ገደብ
እንዳማረ የሚኖር የለም
አታላይ ናት ይቺ አለም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists